TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ🔝ተማሪዎች ግቢው ውስጥ የተፈጠረው ችግር #ሊቀረፍ ባለመቻሉ እና አሁንም በግቢው ውስጥ መቆየት ስጋት ስለሆነባቸው ግቢውን ለቀው ለመውጣት ተደገደዋል። መንግስት ችግሩን በዘላቂነት እንዲፈታም ጥሪ አቅርብዋል። የበርካታ አመታት ልፋታችን ይህ በመሆኑን እናዝናለን ብለዋል።

ፎቶ፦ TIKVAH-ETH(ቤተሰብ አባላት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁመራ🔝በትግራይ ክልል #ሁመራ ከተማ በትላንትናው ዕለት ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፈኞቹ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰብዐዊ መብት ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦችና በሌቦች ላይ የጀመረው ዘመቻ አንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ሰልፈኞቹ በጉዳዩ ላይ የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት የሰጡትን መግለጫ #እንደሚደግፉም ገልጸዋል። ተመሳሳይ ሰልፎች ዛሬ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

ምንጭ:- ኢትዮጵያ ላፕቨ አፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

የተቋሙ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ የተፈጠረው ችግር በዘላቂነት እንዲፈታ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉንም ያካተተ #ውይይት ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ትላንት የተወሰኑ ተማሪዎች ተስማምተው ግቢው ውስጥ ሰላም ወርዶ የነበር ቢሆንም ምሽት ላይ ተማሪ ተጋጭቶ ነበር በዚህም የፀጥታ አካላት እርምጃ ውስደዋል ሲሉ ተማሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መገናኛ ብዙሃን  ከጥላቻና መለያየት ይልቅ በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የሰላም ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ። “ሚዲያ ለሰላም” በሚል አገር አቀፍ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት የፓናል ውይይት ትላንት ተካሂዷል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስራቸውን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል አሳስበዋል። መገናኛ ብዙሃን በህዝቦች መካከል #ግጭቶችን ከመፍጠርና ከማራራቅ ይልቅ አንድነትና መተባበርን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ‼️አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የመኪና ውድድር እየተካሄደ ስለሆነ ወደዛ አካባቢ ያላችሁ ጥንቃቄ እድታደርጉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን!

ከእናንተ ብዙ #እንጠብቃለን። ከግብታዊ እርምጃ ርቃችሁ ለቤተሰብም ሆነ ለአገር #መከታ ሆናችሁ ቀጥሉ። ለመሪነት ራሳችሁን የምታዘጋጁበትን ጊዜ አታባክኑት።

via~Endalamaw Abera
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በሱማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው ግጭት ዳግም አንዳይከሰት የሁለቱ ክልል መንግስታት እየሰሩ መሆኑን የሱማሌ
ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሐመድ_ዑመር ገልፀዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም🔝ዛሬ በአክሱም ከተማ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። በሰልፉ ላይ የከተማይቱ ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

ፎቶ፦ prince(ከአክሱም TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በሰቲት ሁመራ፣ በአድዋ፣ በመኾኒ፣ በአቢ አዲ (ተንቤን) እና በሌሎች የትግራይ ክልል ከተሞች ትዕይንተ ህዝብ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በትዕይንተ ህዝቡ የተሳተፉ ዜጎች "የትግራይ ህዝብን #ለማሸማቀቅ" የሚደረጉ ሙከራዎች እንዲቆሙ፤ የሕግ የበላይነት እንዲከበር የሚጠይቁና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ላይ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia