TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች

° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ ሲቀበል ውሏል።

አርሶ አደሮቹ ፥ " ' ያቀረብንላችሁን ምርጥ ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ ብቻዉን መውሰድ አትችሉም ' መባላችንን ተከትሎ የሚችል እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ሲገዛ የማይችል የዘር ወቅት እያለፈበት ነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የድንች ተከላ ፣ የአደንጓሬ መዝሪያ ፣ የጎመን መትከያ እና የብዙ የክረምት ግዜ አዝመራ ስራ ነው " የሚሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ስለዚህም የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ቢሆንም ይህን ግን ማግኘት አልቻልነም ብለዋል።

በተለይ " ጃለለ የሚባለው ድንች ሞክረነዉ ከኛ አካባቢ ጋር የማይስማማ መሆኑን ተከትሎ ብንተወውም የወረዳው አመራሮች ግን  እንድንዘራዉ እያስገደዱን ነው " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

የአካባቢውን የአርሶ አደሮች ቅሬታ ይዘን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ፍናን አነጋግረናቸዋል።

ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ስንል ጠይቀናል።

እሳቸውም ፤ " ግዳጅ የሚባል ነገር የለም " በማለት አርሶ አደሩ ይሆነኛል የሚለውን ዘር በጁ ካለው ማዳበሪያ ብቻ መውሰድ ይችላል ሲሉ መልሰዋል።

" የማዳበሪያ ስርጭቱን በተመለከተ ነጋዴና ደላላ እጅ እንዳይገባ ጥንቃቄ እያደረግን ቢሆንም የትኛውም መሬቱን ዝግጁ ያደረገ ገበሬ የማዳበሪያ ችግር አይገጥመውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግር ካለም ለመፍታት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አስተዳዳሪው " ዘመናዊ  የግብርና አሰራሮችን መከተልና ምርጥ ዘሮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን " በማለት ይህንም ከወረዳዉ አርሶ አደር ጋር የጋራ መግባባት ተደርሶ እየተሰራበት ነው ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ ° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች ° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ…
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

ሲዳማ !

" የማዳበሪያ ችግር የለም ተብሎ በሚዲያ ቢነገርም በቂ ማዳበሪያ እየደረሰን አይደለም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች

ከሰሞኑ " ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አይሰጣችሁም ተባልን " ያሉ የሀዋሳ ዙሪያ አርሶ አደሮች ቅሬታ ማቅረባቸዉን ዘግበን ነበር።

በወቅቱ  የማዳበሪያ ችግር እንደሌለና ወደግብርና ቢሮ በመምጣት መዉሰድ እንደሚቻል ከምርጥ ዘር ጋር በተያያዘ አርሶአደሩን የሚጠቅም አካሄድ መሆኑን ይሁንና ገበሬዉ የራሱ ዘር ካለዉ እንደማይገደደ ተገልጾም ነበር።

ይሁንና ከመረጃዉ በኋላ " የማዳበሪያ ችግር የለም " ተብሎ በሚዲያ ምላሽ ከመሰጠቱ በላይ በስብሰባ ወቅት " መጋዝናችን ሙሉ ነዉ " ብንባልም በአግባቡ እየተሰጠን አይደለም ሲሉ በድጋሜ የአካባቢዉ አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርበዉልናል።

" አሁን ላይ የዘር ወቅት እያለፈ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ገብተናል " የሚሉት አርሶ አደሮቹ " አራትና አምስት  ኩንታል ለሚያስፈልገዉ አምስት ሄክታር የለሰለሰ ማሳ አንድ ኩንታል ብቻ ስለምን እንደሚሰጠን አይገባንም " በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" ማዳበሪያዉ በቂ አለመሆኑን የአካባቢዉ የግብርና ባለሙያዎች ያውቃሉ። እንደኛ ከማዘን ዉጭ መፍትሄ መስጠት አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዉ ጉዳዩ በአመራሩ እጅ መያዙን አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፥ " ቀኑን ሙሉ ስራ በመፍታት መጋዝን በር ላይ የሚዉለዉ አርሶ አደር ሀያ ሰላሳ ሰዎች ከተስተናገዱ በኋላ ወደቤታችሁ ሂዱ ይባላል በማለት መጋዝኑን የሞላዉ ማዳበሪያ ለማን ነዉ ? " በማለት ጠይቀዋል።

ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " የማዳበሪያ ችግር የለም ከአካባቢዉ አርሶ አደር ጋርም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል " ያሉት የወረዳዉ አስተዳዳሪ  " መሬቱን ያዘጋጀ ገበሬ የፈለገዉን ያክል ማዳበሪያ መዉስድ ይችላል " በማለት አንዳች ቅሬታ ያለበት አርሶ አደር ካለ ሊያናግረን ይችላል ማለታቸዉ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM