TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የቀድሞው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ አራት ባለሥልጣናት ዛሬ ችሎት ቀርበዋል።

ከአብዲ ኢሌ በተጨማሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት፦

📌የቀድሞ የክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ #ራህማ_ማህድ ሀይቤ፣

📌የቀድሞ የክልሉ የዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ #አብዱረዛቅ_ሳኒ

📌የቀድሞ የክልሉ የመስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ #ሱልጣን_መሐመድ

ተጠርጣሪዎቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል #ዘርና #ብሔርን ለይተው የክልሉን ወጣቶች #አስታጥቀው ለበርካቶች ሞትና መፈናቀል እንዲሁም ለሃይማኖት ተቋማት ውድመት ምክንያት ሆነዋል በሚል ነው፡፡

ፖሊስ ለምርመራ 15 ቀን ጠይቋል፡፡
ሁሉም ተጠርጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀል።

‹‹ፖሊስ ለምርመራ የጠየቀው ጊዜ በዝቷል፣ እስካሁን #ቃላችንን አልተቀበለም፤ ነገር ግን ከተያዘን 48 ሰዓት አልፏል›› ሲሉ ተደምጠዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia