TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update MTN⬆️

ፕሬዚዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ ከኤምቲኤን የስራ ኃላፊዎች ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ መሰማራት በሚችልበት ሁኔታ ተወይተዋል።

ኩባንያው የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ለማዞር እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱ ተነግሯል።

ምንጭ፦ አሀዱ FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምስተኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ነገ ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሙላቱ_ተሾመ በሚያደርጉት ንግግር በይፋ እንደሚጀምር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ንግግር ተከፍቷል። ፕሬዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ ዛሬ ባደረጉት ንግግር ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዓብይ_አህመድ እና ለኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ #ኢሳያስ_አፈወርቂ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

የአምና ወይም 2010 #የወርቅ_ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች እስካሁን ስኮላርሺፕ እንዳላገኙ ለTIKVAH-ETHIOPIA በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የወርቅ ሜዳሚያ ተሸላሚ ተመራቂዎቹ እንዳሉት፦ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ ቃል በገቡልን መሰረት ውጪ ሀገር scholarship እንደ ሚሰጠን በሁሉም የሚዲያ የተነገረ ነበር። ፕሬዘዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ በበኩላቸዉ የውጪ ሐገር scholarship ባይሳካ ሐገር ውስጥ ታገኛላቹ ተብለን ነበር። ነገር ግን እስከ አሁን ምንም ነገር የለም። በተለያየ ሚዲያ እንዳገኘን ሲወራ ነበር። በተደጋጋሚ ትምርት ሚኒስቴር Dr. ጥላዬን እና ዶክተር #ሳሙኤልን ብንጠይቅም #መልስ ሊሠጡን አልቻሉም።" ብለዋል። ብዛታቸው 395 አካባቢ እንደሚሆን የተናገሩት ተመራቂዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ ፕሬዘዳንት‼️

የኢፌዴሪ አዲስ ፕሬዝዳንት ነገ ይሾማሉ። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ።

ምክር ቤቶቹ በስብሰባቸው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ሙላቱ_ተሾመ የሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል #አዲስ ፕሬዚዳንት #ይሾማሉ

ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት ነበር አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን በመተካት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት።

ሶስተኛው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ነገ ለሚተካቸው አራተኛ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት በምክር ቤቶቹ ፊት ስልጣን ያስረክባሉ።

ምንጭ፦ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia