TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በነፍስ ግድያ፣ ከቀዬ በማፈናቀል፣ በአስገድዶ ማስደፈር፣ የሃይማኖትና የንግድ ተቋማትን በማቃጠል፣ በዝርፊያና በሌሎች በርካታ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው የታሰሩት የቀድሞ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #አብዲ_ኢሌ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስቀመጡት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ታገደ፡፡

#REPORTER
#Breaking ባለቤትነቱ የትራንስፖርት ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ #መከስከሱ ታውቋል።

Via #reporter
ፎቶ-የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚድሮክ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ‼️

ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መከስከሱ ታወቀ፡፡ በበረራው ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰም ከምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ በሚድሮክ ቴክኖሌጂ ግሩፕ ሥር የሚተዳደር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት የዚሁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር በቦሌ አካባቢ መከስከሱ ይታወሳል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ👆ዛሬ ጥዋት የተከሰከሰው ሂሊኮፕተር የወደቀው በመኖሪያ ቤት ላይ ሲሆን፤ የተከሰከሰበት ምክንያትም የሞተር መጥፋት እንደሆነ ነው የታወቀው።

#reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ ቴሌኮም ሃብቱን በውጭ ኩባንያ እያስመረመረ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ መርማሪው የእንግሊዙ ፕራይስ ወተር ሃውስ ኩፐር የተባለው ኩባንያ ነው፡፡ ኩባንያው ካሁን በፊት የኢትዮ ቴሌኮምን የፋይናንስ አስተዳደርና የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት አደራጅቷል፡፡ ጥናቱ እስከ 6 ወራት ሊፈጅ ይችላል፡፡ የሃብት ግምቱ ሲጠናቀቅ ዲሊዮት የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያና ኧርነስት ኤንድ ያንግ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ደሞ ኢትዮ ቴሌኮም በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለሃብቶች ሲዘዋወር የአክሲዮን አወቃቀርና ሽያጭን በተመለከተ እንዲያማክሩ ተቀጥረዋል፡፡ የአማካሪ ኩባንዎችን ወጭ ዐለም ባንክና ለጋሽ ሀገራት ይሸፍናሉ፡፡ አጠቃላይ ሂደቱ የሚመራበት ረቂቅ ሕግ ገና በፓርላማ አልጸደቀም፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል...

የአማራ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ፣ አራት የክልሉ አመራሮች መታሰራቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሱት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለዕድለኞች መተላለፍ ጀመሩ፦
.
.
የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በነበሩት አቶ ጃንጥራር ዓባይና በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋላ፣ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሮ የነበረው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ማስተላለፍ ተጀመረ፡፡

ከ18 ሺሕ በላይ በሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከወጣ በኋላ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በገቡት ውል ምክንያት በወቅቱ እንደ ቤቱ ስፋት ተተምኖ የነበረውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ (መቶ በመቶ) የፈጸሙ በርካታ ሰዎች የዕጣውን መውጣት ተቃውመው ነበር፡፡ ተቃውሟቸው ‹‹ለምን ዕጣው ወጣ?›› በሚል ሳይሆን፣ ከንቲባው የቤት ግንባታ ፕሮግራም ዓላማና መመርያ ከ40 በመቶ በላይ የተገመተውን ዋጋ የቆጠበ በሙሉ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ መካተት አለበት ብለው ዕጣው በመውጣቱ ነበር፡፡

በመሆኑም መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙት በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውት ነበር፡፡ ከ200 በላይ የሚሆኑ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መቶ በመቶ ከፋዮች፣ በተለያዩ መዝገቦች የዳኝነት በመክፈል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክስ መሥርተው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝን የከሰሱት ግለሰቦቹ፣ ባንኩ ውል በመፈጸም ሚኒስቴሩ ያወጣውን መመርያ ባለማስፈጸሙና ኢንተርፕራይዙ ደግሞ ሕግ ተላልፎ ዕጣ በማውጣቱ፣ በአንድ ላይ በመክሰሳቸው ፍርድ ቤቱ ዕጣ የወጣባቸውና ዕጣ ያልወጣባቸውም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች እንዳይተላለፉ ዕግድ ጥሎ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ክስ ከመረመረ በኋላ በሰጠው ትዕዛዝ፣ በተለይ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች የተመዘገቡት የቤት ዓይነት ከየሳይቱ ታግዶ እንዲቆይ በማለት፣ የቀሪዎቹን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ አንስቷል፡፡

ሌሎችም አመልካቾች በተመሳሳይ ሁኔታ ክስ መሥርተው ጉዳያቸው እየታየ ቢሆንም፣ ዕግዳቸው የተነሳላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ከሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ውል የሚዋዋሉበት ፕሮግራም በየክፍላተ ከተሞቹ ወጥቶላቸው በመዋዋል ላይ ይገኛሉ፡፡

አስተዳደሩ 32,653 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ያወጣ ቢሆንም፣ ለዕድለኞቹ መቼ እንደሚተላለፉ ያለው ነገር የለም፡፡   

Via #reporter
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት...

የአ/አ ከተማ አስተዳደር 32,653 የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ያወጣ ቢሆንም፣ ለዕድለኞቹ መቼ እንደሚተላለፉ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡   

Via #reporter
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ታስረው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

አቶ ክርስቲያን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ታስረው የሚገኙ የአብን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ጠይቀው ሲመለሱ መሆኑን የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አመራሮቻቸውና አባሎቻቸው የታሰሩት በቀዝቃዛ ቦታ፣ የፀሐይ ብርሃን በማያገኙበትና ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በማይችል ሁኔታ በመሆኑ እንዲሻሻልላቸው ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተው ሲወጡ፣ መውጫ በር ላይ አቶ ክርስቲያንን እንደያዟቸው ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው መርማሪ ፖሊስ በነጋታው ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ፣ ምድብ ወንጀል ችሎት እንዳቀረባቸውም አስረድተዋል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ለምን አቶ ክርስቲያንን በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና እንዳሰራቸው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ ተጠርጣሪው ወጣቶችን መሣሪያ እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ በማስረዳት ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት መጠየቁም ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ክርስቲያንም ወጣቶችን መመልመልና ማደራጀት ሥራቸው መሆኑንና ከእስርም ሲለቀቁ የሚቀጥሉት ሥራቸው እንደሆነ ተናግረው፣ መሣሪያ ያስታጥቃሉ ስለተባለው ግን ፖሊስ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ፖሊስ ምርመራውን እንዲያጠናቅቅ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዛን_ንግድ

20 ሺ ሠራተኞችን #ለመቅጠር ገንዘብ እያስከፈለ በመመዝገብ ላይ የነበረው ግለሰብ ከእነ ጓደኞቹ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አብዛን የተሰኘ የንግድ ሥራ ድርጅት ባለቤት መሆኑ የተገለጸ ግለሰብ 20 ሺሕ ሠራተኞችን ለመቅጠር በነፍስ ወከፍ 2,477 ብር በማስከፈል፣ በርካታ ወጣቶችን በመመዝገብ ላይ እያለ ከጓደኞቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ውሎ ታሰረ፡፡ግለሰቡ አቶ አብርሃም ዘሪሁን የሚባል ሲሆን፣ የሥራ ማስታወቂያውን በቃና ቴሌቪዥንና በሌሎች ሚዲያዎች በማስተዋወቅ፣ ከሐምሌ 1 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ እያንዳንዱ ተመዘጋቢ የ2,477 ብር ሲፒኦ አሠርቶ እንዲመዘገብ ጥሪ ማድረጉ ታውቋል፡፡
.
.
ተጠርጣሪዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና በተለይ የ2011 ዓ.ም. ተመራቂ ወጣቶችን በማማለል ከሦስት ሺሕ ብር በላይ ደመወዝ እንደሚከፍል፣ #ሐሰተኛ ማስታወቂያ በማስነገር ከእያንዳንዱ ተመዝጋቢ 2,744 ብር መቀበላቸውን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ስለማስታወቂያውና ስለሥራው የተጠራጠረው ፖሊስ ከአሥር ተመዝጋቢዎች ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጥርጣሬውን ይበልጥ ስላጎላው፣ ግለሰቦቹን ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑንና ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ABZAN-07-24

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዕርዳታ ያሰባሰበውን 116 ሚሊዮን ብር (አራት ሚሊዮን ዶላር)፣ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች እንደመደበ አስታውቋል፡፡

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia