TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GONDAR : ጥብቅ ማሳሰቢያ !

በጎንደር ከተማ የሚገኙ ሁሉም የህትመት ድርጅቶች ከከተማ አስተደደሩ እዉቅና ኖሮት እስካልተፈቀደ ድርስ ከየትም ቦታ የመጣ ማንኛዉም የመታወቂያ ህትመት እንዳይሰራ ከተማ አሰተዳደሩ በጥብቅ አሰስቧል።

@tikvahethiopia
#Gondar : ዛሬ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የመስቀል በዓል ተከብሯል።

በዓሉ በልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው የተከበረው።

ፎቶ : HENA (Gondar Tikvah Family)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዋሪዎችን ያማረረው ህገወጥ ተኩስ... በጎንደር ከተማ በተለይም ማራኪ ክፍለ ከተማ ሰሞኑን የተለያዩ ምክኒያቶች ስበብ በማድረግ ህገ ወጥ ተኩስ እየተፈጸመ ይገኛል። ይህን ምክኒያት በማድረግ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ትላንትናው ውይይት አድርገዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በአካባቢያቸው የሚፈፀመውን ህገወጥ ተኩሱን አውግዘዋል። የጦር መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች የወታደራዊ የጦር መሳሪያው አያያዝ ህግና…
#GONDAR : በጎንደር ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ የከተማው ፖሊስ መሳሪያ የማስወረድ ስራ እና ሰዎችን የማሰር እርምጃ እየወሰደ ነው።

ከትንላት ጀምሮ እስከ አሁን ሰአት ድረስ የጎንደር ከተማ ፖሊስ ከ50 የሚበልጥ የጦር መሳሪያ ያስወረደ ሲሆን ከህገወጥ ተኩስ ጋር በተያያዘ ከ30 በላይ ሰዎችን ማሰሩንና ፍ/ቤት በማቅረብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ለጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

ስራው እየተሰራ የሚገኘው ከፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል እንዲሁም ከከተማው የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮችን ባካተት ቡድን ነው ተብሏል።

የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ማምሻውን ለጎንደር ኮሚኒኬሽን በሰጡት ቃል፤ " ያለአግባብ መሳሪያ ሲተኩሱ የነበሩና ከህግ ለማምለጥ የተደበቁ ግለሰቦችንም የገቡበት ገብተን በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራ እየተሰራ ነው" ብለዋል።

ኮማንደሩ አክለው ፥ "ህብረተሰቡ የሚሰጠውን ማንኛውም ጥቆማ በመቀበል ቦታው ድረስ የፀጥታ አካላትን በመላክ ህግ የማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ያሉ ሲሆን "ህብረተሰቡ ይህን ተረድቶ ትብብሩን ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የህገ ወጥ ተኩስ ጉዳይ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በእጅጉ ሰላም የነሳቸው እና ያማረራቸው ጉዳይ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለፅ እንደነበር ይታወቃል ፤ ከጊዜ ወደጊዜ ይህ ድርጊት ይቆማል ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በተለያየ ጊዜ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#Gondar : አቶ ዘውዱ ማለደ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።

ዛሬ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው ጉባዔ አቶ ዘውዱ ማለደን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

ም/ቤቱ የ4ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ አጀንዳዎች መርምሮ ያፀድቃል ፤ ተጨማሪ ሹመቶችንም እንደሚያፀድቅ የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#GONDAR

" ለመንገድ ስራ ደማሚት ይፈነዳል፤ እንዳትደናገጡ " - የጎንደር ፖሊስ

ከዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከኮሌጅ ብሪጋታ የመንገድ ስራ ለመስራት ደማሚት ይፈነዳል፡፡

ነዋሪዎች ጉዳዩን አውቀው ያለ ምንም መደናገጥ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ መልእክት አስተላልፏል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#GONDAR : በጎንደር ከተማ ህግ ተላልፈዋል የተባሉ 53 የፀጥታ አካላት እንዲጠየቁ መደረጉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፀ።

መምሪያው ይህ ያሳወቀው በመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ አማካኝነት ለከተማው ነዋሪዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመወያያ ፅሁፍ ባቀረበበት ወቅት ነው።

በከተማዋ የእገታ ወንደል ህገ ወጥ የጥይት ተኩስ ተጀራጅቶ ዘረፉ ዋና ወና የከተማዋ ወንጀሎች መሆናቸውን አቶ ፋሲል ገልፀዋል።

በዚህ የእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ 34 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

4 በእገታ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑም ጠቅሰዋል።

በከተማዋ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉት 14 በየደረጃው በሚገኙ የፀጥታ አመራሮች 20 የፓሊስ አባላትና 14 የሚኒሻ አባላት ተጠያቂ መሆናቸውም አሳውቀዋል።

የመስቀል በዓልን ምክኒያት በማድረግ ጥይት ተኩሰዋል የተባሉ 115 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

የከተማዋን ፀጥታ በመጠበቅ ረገድም ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዎ የሚበረታታ ነው የተባለ ሲሆን የጀመረውን የሰላም የፀጥታ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተብሏል።

መረጃው የጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#GONDAR : ፖሊስ በጎንደር ከተማ ለእኩይ/ለሽብር ተግባር ሊውል ነበረ ያለውን ገጀራ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

ገጀራው በከተማው ቀበሌ 16 በተለምዶ ግሩፕ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግለሰብ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተገኘ ነው ተብሏል።

ማህበረሰቡ ባደረሰው ጥቆማ ከአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገወጥ ገጀራው መገኘቱን ያስረዳው የከተማው ፖሊስ ጥቆማ የተሰጠባት ግለሰብ ቤት ፖሊስ ሄዶ ህገወጥ ገጀራ መኖሩን ሲጠይቅ ምንም ነገር እንደሌለ መግለጿ ተመላክቷል።

ነገር ግን በተደረገው ፍተሻ በአልጋ ስር በከፍተኛ ሁኔታ የተደበቁ ገጀራዎች መገኘቱን እና ገጀራው ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ያልዋለና ለእኩይ አላማ ሊውል እንደታሰበ ያመለክታል ብሏል ፖሊስ።

የጎንደር ፖሊስ አሁን ላይ ነባራዊ ሁኔታውን መሰረት ባደረገ ሁኔታ በሮችን ከሁሉም የፀጥታ ኀይል ጋር በመሆን 24 ሰዓት እየጠበቀ መሆኑን ወንጀልንና ወንጀለኞችን መከላከልና መቆጣጠር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በቀጣይም ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን መሰል ህገወጦችን በቁጥጥር ስር እያዋልነ ወደ ህግ የማቅረብ ተግባሩ እንደሚቀጥል አሳቋል።

ምንጭ ፦ የጎንደር ከተማ 4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል

@tikvahethiopia
#GONDAR

በጎንደር ከተማ በፋሲል ክፍለ ከተማ በአንድ ሪስቶራንት ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ሬስቶራንቱ ወደመ።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢስፔክተር ስማቸው ፈንታ እንደገለፁት በከተማዋ በፉሲል ክፍለ ከተማ ከቀኑ 8 ስዓት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የሪሴቶራንቱ ቁሳቁስ የወደመ ሲሆን የእሳት አደጋው ምክኒያት እየተጣራ መሆኑን እንስፔክተር ስማቸው ገልፀዋል።

ከሪስቶራንቱ የተነሳው የእሳት አደጋ በዙሪያው ያሉ ቤቶች መጠነኛ ጉዳት ቢደርስም በፀጥታ አካላትና በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ የእሳት ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን ኢንስፔክተሩ ገልፀዋል።

በእሳት አደጋ መከላከል ስራው ላይ የነበረ አንድ ግለሰብ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እየተደረገለት መሆኑ ጠቁመዋል።

መረጃው የጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#GONDAR

ዛሬ ከሁመራ አድርጎ ወደ ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ያለ ተሳቢ መኪና ተገልብጦ ሹፌሩን ጨምሮ የ5 ሰዎች ህይወት ጠፋ።

አደጋው በጎንደር ከተማ በፋሲል ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኩረበረብ ተብሎ እሚጠራው አካባቢ ቀን 8:30 ገደማ የደረሰ ሲሆን 2 ወንድ እና 3 ሴቶች ህይወታቸው ሲያልፍ 3 ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የማህበሰረብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ም/ ኢንስፔክተር ስማቸው ፈንቴ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara , #Gondar 📍

በጎንደር ከተማ ሳይታገት " ታግቻለሁ " ብሎ ያስነገረው ግለስብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፓሊስ አስታወቀ።

ግለስቡ ከየካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መታገቱን ለቤተስቦቹ በመግለፁ ቤተስቦቹ ለፓሊስ በማመልከታቸው ፓሊስ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል።

የካቲት 5 ቀን 2014ዓ.ም በፀጥታ አካላት ክትትል ደባርቅ ከተማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ግለሰቡ በተያዘበት ወቅት ካርታ ሲጫወት የተገኘ ሲሆን፤ ሁለት ግለሰቦች በሰጡት ቃል ግለሰቡ ብቻውን እንደመጣ እና በነፃነት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ገልፀዋል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ የአንደኛ ፓሊስ ጣቢያ ግለስቡ ጠፍቷል ከተባለበት ዕለት ጀምሮ ፓሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት ክትትል ሲያደርጉ መቆየቱን እና ግለስቡ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

የወንጀሉ ድርጊቱን ለማጣራትም የምርመራ ቡድን ተደራጅቶ የማጣራት ስራ እየተስራ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

በጣቢያው ከዚህ ቀደም ሳይታገት ታግቻለሁኝ ያለ ግለስብ እንደነበር የጠቆመው ፖሊስ ህብረተስቡ ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠብ መልክት አስተላልፏል።

ምንጭ፦ ጎንደር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia