TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን⬆️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #በስራ እንቅስቃሴዎቻቸው ጎልተው በመውጣት ከተጠርጣሪዎች #የገንዘብ መደለያ #አንቀበልም ሲሉ ለህግ በማቅረብ ለሰሩት #አኩሪ ተግባር ለአመራርና ለአባላቱ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ በሀገር #ደህንነት እና #ሰላም ጉዳይ ላይ #ጠንካራ ውሳኔዎች እንደሚያሳልፍ እምነቴ ነው። ከዚህ በኋላ ችግር እና መከራ የምንሰማበት ጊዜ ማብቃት አለበት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀረር⬇️

"ካኑቺ ነኝ! በሐረር ከተማ ህዝቡን በአስከፊ ሽታ ለበሽታ የዳረገው በተለይም #የሸዋበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለወራት የተጠራቀመው የቆሻሻ ክምር ዛሬ #በመነሳት ይገኛል፣ በሌሎች አካባቢዎችም ያለውን የቆሻሻ ክምር የማንሻ ሰዓት ወደ ማታ ቢሆን፣ ምክንያቱም በሚነሳበት ወቅት በፀሐይ አማካኝነት የሚወጣው ሽታ ሊገበያይ የመጣው ነዋሪ ከሚገበያየው እቃ በተጨማሪ የበሽታም ሸማች ያደርገዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ የኢህአዴግ ጉባኤ⬇️

ኢህአዴግ በ11ኛው ጉባኤው #በርዕዮተ_ዓለም ለውጥ ላይም ሆነ በአርማ ለውጥ ላይ #እንደማይወያይ ተገልጿል። የጉበኤውን ውሎ በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የጉባኤው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንደገለፁት ጉባኤው አጀማመሩ ያማረና ከሌላው ጊዜ በበለጠ በርካቶችን ያሳተፈ ነበር ብለዋል።

የተፎካከሪ ፓርቲዎች መሳተፍ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የእስያ ሀገራትን የወከሉ የፓርቲ አመራሮችም በመክፈቻው መገኘታቸው ጉባኤውን #ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

ጉባኤው ከመክፈቻ ፕሮግራሙ በኋላ በጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ የቀረበለት ሪፖርት ላይ መወያየቱን እና ይህ በነገው ዕለትም እንደሚቀጥል ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ጉባኤው በቆይታው የሚመክርባቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በርዕዮተ ዓለም ለውጥም ሆነ በስምና አርማ ለውጥ ላይ እንደማይመክር ግን ቃል አቀባዩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH🙏ባለፉት 5 ቀናት ብቻ ወደቻናላችሁ የመጣችሁ 4 ሺ (4000) ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደህና መጣችሁ!

ውጤቱ የናተው ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ አፍሪካው ኤ ኤን ሲ ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት በሴቶች ላይ #ወሲባዊ ጥቃት የፈፀሙ ወንዶች የዘር ፍሬያቸው #እንዲኮላሽ የሚያዝ ሕግ ተግባራዊ እንዲሆን ደገፉ፡፡

©ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ እና ትብብር‼️

(በአፋጣኝ ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከቤኒሻንጉል ተፈናቅለው በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ለሚገኙ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን እርዳታ ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ እና አካባቢው ለሚኖሩ ወገኖቻችን ባቀረብነው የእርዳታ ጥሪ፤ በርካታ ወገኖቻችን መልዕክቱን ሼር በማድረግ ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ በሀገር ፍቅር የሚኖረውን የቁሳቁስ፣ አልባሳትና ምግቦች እርዳታ ከሰኞ ቀደም ባሉ ቦታዎች ግዚያዊ መረከቢያ #ጣቢያዎች እንዲኖሩ አብዛኛዎቻችሁ ጠይቃችኋል።

በዚህም መሰረት ከነገ ሐሙስ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ፤ በሁሉም አቅጣጫ ግዚያዊ መረከቢያ ጣቢያዎች እና #ማስተባበሪያ ማዕከሎችን እናዘጋጃለን። ለዚህም የመረከቢያ ቦታ ችግራችንን ለመፍታት ይቻል ዘንድ ፍቃደኛ የሆናችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
በየሰፈራችሁ ምቹ የሆነ መረከቢያ ቦታ በመፍቀድ እንድትተባበሩን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

* ቦታው ቢቻል ለምልክት ግልጽ የሆነ ቢሆንና ከዝናብና ፀሐይ ውጪ መሆን የሚችል ቢሆን ይመረጣል።

*ለትራንስፖርት አመቺ ቢሆን መልካም ነው።

*የንግድ ድርጅቶችና ተቋማትም መሆን ይችላሉ።

*የተሰበሰቡት ንብረቶች በሙሉ ወደ ዋናው መረከቢያ ጣቢያ (ሀገር ፍቅር ቴአትር) ተሰባስበው የሚገቡት ሰኞ እና ማክሰኞ በመሆኑ ቦታችሁን የምትፈቅዱልን በሙሉ እስከ ሰኞ ድረስ የእርዳታዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ የማትቸገሩ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ትከቱልን ዘንድ እንለምናለን።

~በዚህ መሰረት ፍቃደኛ የሆናችሁ በሙሉ በቀጣዩ ስልክ ቁጥር ~ 0930 36 52 44
መሐመድ ካሳ እና ያሬድ ሹመቴ ብላችሁ ፈጣን ትብብራችሁን እንድትገልፁልን በማክበር እንጠይቃለን።

(በተደጋጋሚ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃለፊነታችንን እንወጣ ዘንድ እንለምናለን)

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት!!

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለልጆቻችን ስንል የአያቶቻችንን መጥፎ ታሪክ #በይቅርታ እንዝጋው!

አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ #ዝግ ነው።

ፎቶ፦ Do(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌ቦሌ መንገድ በሚገኘው የፓርላማ አባላት መኖሪያ አፓርታማ አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ #የተኩስ ልውውጥ የነበረ ሲሆን፣ የቦሌ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱና የሰው #ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከእስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ተከፍቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተኩስ ልውውጡ ምክንያት በአፓርታማው ጠባቂ(ፌደራል ፖሊስ) እና በሌሎች የፌደራል ፖሊሶች መካከል የተፈጠረ #አለመግባባት እንደነበረና በተኩስ ልውውጡም 2 አባሎች #ህይወታቸው ሲያልፍ 4 አባሎች ላይ #ቀላል ጉዳት መድረሱን ኮማንደር ብርሃነ ለetv በስልክ መስመር ገብተው ገልፀዋል። #በነዋሪዎች ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም።

ቦሌ መንገድ በሚገኘው የፓርላማ አባላት መኖሪያ አፓርታማ አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የቦሌ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱ ታውቋል። እንዲሁም ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድም ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር። አሁን ላይ መንገዶቹ መከፈታቸው ተከፍተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ (ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ), ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል #በመጠጥ ሀይል ተገፋፍቶ በባልደረቦቹ ላይ #ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ለfbc እንደተናገሩት፥ የፌደራል ፖሊስ አባሉ በባልደረቦቹ ላይ በፈፀመው ጥቃትም ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት #ህይወት አልፏል።

ፖሊስ ጥቃቱን ለማስቆም በወሰደው እርምጃም ጥቃቱን የፈፀመው የፌደራል ፖሊስ አባል ህይወቱ ማለፉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅም በስፍራው ተስተጓጉሎ የነበረው የትራፊክ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
LTV! ትላንት ምሽት ቤቲ ከዶክተር ደሳለኝ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ያልተከታተላችሁ አሁን መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
MTN