TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባን ከመቀለ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በአማራና በትግራይ ክልሎች ድንበር ላይ #በመዘጋቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ ተገቷል።

ምንጭ፦ ETHIOPIA LIVE UPDATE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

የቦንጋ መንገድ መስመር #በመዘጋቱ መንገደኞች እየተቸገሩ እንደሆነ ጠቁመዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካል ችግሩን እንዲፈታም ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባቢሌ ላይ መንገድ ተዘግቷል‼️

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናገሩ።

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

በሐረር ከተማ በሚገኘው መናኽሪያ ኢዜአ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች እንደሚገልጹት ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ መንገዱ በመዘጋቱ ተሽከርካሪዎቻቸውን ለማቆም ተገደዋል።

የመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪው አቶ ዘላለም አማረ እንዳሉት ከትላንት አመሻሽ ጀምሮ መንገዱ በመዘጋቱ ወደ ሐረር ከተማ ለመመለስና ያለ ስራ ለመቀመጥ ተገደዋል።

በአካባቢው የተፈጠረውን ችግር መንግስት ተመልክቶ በአፋጣኝ በመፍታት ስራቸውን የሚጀምሩበት ሁኔታ እንዲመቻችም ጠይቀዋል።

“ህዝቡ መንግስት የመልካም አስተዳደርና የመብት ጥያቄን በአፋጣኝ ምላሽ አልሰጠም በሚል በየከተማው መንገድ መዝጋት የተለመደ ተግባር እየሆነ ነው” ያሉት ሌላው አሽከርካሪ አቶ አፈንዲ አሊ “ሁኔታውም እየተለመደና እየተደጋገመ ስለሚገኝ ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል”ብለዋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሐላፊ ኮማንደር አወል ሱልጣን እንደተናገሩት ባቢሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በተፈጠሩ ችግሮች ተፈናቅለው በባቢሌ ከተማ የሚገኙ ዜጎች ዘላቂ  መፍትሔ ይሰጠን በሚል መንገዱን ሊዘጉ ችለዋል።

“ይህንንም ችግር ለመፍታት የዞን አመራርና የጸጥታ ሐይል ከአገር ሽማግሌዎችና ከሌሎች አካላት ጋር በጋራ በመሆን ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል” ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 24/2011 ዓ.ም.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ።
.
.
የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።
.
.
ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሹመዋል።
.
.
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ጊዜ ለልማት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ122 ኢንተርፕራይዞች ላይ #እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
.
.
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
.
.
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
.
.
24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቋል።
.
.
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
.
.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
.
.
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡
.
.
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡
.
.
የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
.
.
የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
.
.
የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
.
.
የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡
.
.
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣etv፣fbc፣ ዋዜማ ራድዮ፣ BBC አማርኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia