TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጎንደር‼️

በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናገሩ። ከጎንደር ወደ ገንደውሐ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞችን ያገቱት የመቃ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው ተብሏል። ታጋቾቹ ሌንጫ በተባለ ቀበሌ ጉባይ ጀጀቢት ወደተባለ ቦታ ተወስደዋል። ከታጋቾቹ መካከል ሁለት ልጆች የያዙ አንዲት እናት እንደሚገኙበት በቦታው የነበሩ የዐይን እማኝ ተናግረዋል። መቃ ከተማ በታገተው ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ የሚናገሩት መምህር ጋሻው ጌቴ «ትናንት ከጎንደር ተነስተን ወደ ገንደውሐ ከተማ ስንሔድ መቃ አካባቢ መኪናውን አግተው ከ17 ያላነሰ ሰው ነው ጉባይ ጀጀቢት ወደሚባል ቦታ ይዘውት የሔዱት» ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር እና ጸጥታ ኃላፊ አቶ #ደሳለኝ_ጣሰው እገታው መፈጸሙን ቢያረጋግጡም ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

በተለምዶ አባዱላ ተብሎ የሚጠራው የሕዝብ መጓጓዣ መቃ በተባለችው ከተማ ነዋሪዎች ሲታገት 20 ገደማ ሰዎች ጭኖ እንደነበር መምህር ጋሻው አስረድተዋል። ተሽከርካሪው መቃ ከተማ ላይ ሲደርስ መምህር #ጋሻው_ጌቴን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ወርደው ወደ ሕዝብ በመቀላቀል ማምለጣቸውን የዐይን እማኙ አስረድተዋል። ኩነቱ በአካባቢው በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ የተከሰተ መሆኑን የተናገሩት መምህር ጋሻው እገታውን የፈጸመው «መቃ የሚባል ቀበሌ ሕዝቡ ነው» ብለዋል። የዐይን እማኙ እገታው በተፈጸመበት ወቅት «በጣም ብዙ ሰው ተደብድቧል። በጣም ብዙ ሰው ተመቷል» ሲሉ አስረድተዋል። «ሰዎቹ ይሙቱ ይዳኑ የሚታወቅ ነገር የለም። መኪናው ግን በመከላከያ ተይዟል የሚል መረጃ አግኝቻለሁ» ሲሉም አክለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia