TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጋምቤላ⬆️የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ሊቀመንበር #ኦባንግ_ሜቶ ከ16 ዐመታት ጋምቤላ ተብተዋል። ኦባንግ ጋምቤላ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቡራዩና አካባቢው ለንጹሃን ሞትና ንብረት ውድመት #ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተያዙ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 200 ደርሷል። (ፖሊስ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወንጀለኞቹን መያዝ ብቻ በቂ አይደለም። ማን እንዳሰማራቸው፤ እንዴት እንደተደራጁ፤ ምን አይነት ውይይት እንዳደረጉ፤ በግልፅ ለህዝብ #ይፋ ይውጣና እንደ ህዝብ እንማርበት።" ሰለሞን ደቻሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
etv⬆️ከላይ የሚታየው ፎቶ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈፀመውን ድርጊት ለማውገዝ እና ያላቸውን ተቃውሞ ለማሰማት ያካሄዱት ሰልፍ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኮልፌ⬇️

"አሁን ፊሊጶስም ሾላም ለሰው ጥሩ ነገር ተደርጎላቸዋል። ከተለያየ ቦታ ነው ምግብ እና የሚጠጣ ነገር እንዲሁም አልባሳት እየመጣ ያለው አመስግንልን! ኮልፌዎች!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቁር አንበሳ⬆️በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈፀመውን ወንጀል በመቃወም የአዲስ አበባ ነዋሪ ሰልፍ እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። ከላይ ያለው ፎቶ የጥቁር አንበሳ አካባቢን ገፅታ የሚያሳይ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ⬆️በአሸዋ ሜዳና በተለያዩ አካባቢዎች የጠፈጠረው ግድያና ዝርፊያን #በመቃወም መንግስት ፍትህ ይስጠን በማለት በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው። ፌደራል ፖሊስና መከላከያ በአንዳንድ ቦታ ላይ #እርምጃ እየወሰዱ ነው።

©ይህ ዘገባ የአሀዱ FM ነው!
@tsegabwolde
#Update የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቡራዩና በመዲናዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የተከሰቱ #ግጭቶች ላይ የደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ቡድን #ከዛሬ ጀምሮ መሰማራቱን የኢትዮጰያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህንን ያለው በዛሬው ዕለት ግጭቱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኀን በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫው ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር እንደተናገሩት በደረሰው ግጭት በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን አንስተዋል።

ግጭቱ በዚሁ ከቀጠለ #ለከፋ ጉዳት ያደርሳል ያሉት ኮሚሽነሩ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም እና ተዘዋውሮ የመስራት እንዲሁም በሰላም የመኖር መብቶችን ለማስከበር ጠንከር ብሎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ እስከ አሁን የደረሰውን ጉዳት መንስዔ፣ ጉዳት እና ስፋት አጣርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፖርት በማድረግ ያጠፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋልም ተብሏል።

በተለያዩ ቦታዎችም የተከሰተውን ግጭት እንዲረጋጋ ከመንግስት ጋር እየሰራ መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በመግለጫው የፌደራል እና የክልል #ጸጥታ አካላትም ሚናቸውን #በአግባቡ እንዲወጡ አሳስቧል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fana Live! የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌ፌደራል ፖሊስ ጥብቅ እርመጃዎችን እንደሚወስድ አሁንም #እየወሰደ እንደሆነና ከተቻለ ጥፋታኛን መያዝ የፖሊስን ጠመንጃ የሚነጥቁትን በህግ ስር ለማዋል እንደሚሞከር ከዚህ በዘለለ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገለጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

የህዝቡን #ደህንነት እና #ሰላም ለመጠበቅ ሲል መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትእግስት #ገደብ እንዳለው በመግለፅ #ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ እየተስተዋሉ ያሉት #ሁከቶች #በሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ስም የተቀነባበሩ መሆናቸውን ኮሚሽነር ጀነራሉ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሦስት ቀናት በቡራዩና አካባቢው ብዛት ያላቸው ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በመጠቆም፥ በተለያዩ ቦታዎች ተዘርፈው የነበሩ ንብረቶችን የማሰባሰብ ስራ መሰራቱንም ነው ያስታወቁት።

በአጠቃላይም በቡራዩ ከ300 አስከ 400 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ሲያዙ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ300 በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ #ገንዘብ ተከፍሏቸው ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት እንዲሁም ብሄርን መሰረት ያደረጉ ስድቦችንም ጭምር በማሰራጨት #የተጠረጠሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም አንስተዋል።

ይህ ድርጊት #በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባና በአርባ ምንጭ መታየቱን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽነሩ በቡራዩና አካባቢው የተፈፀመውን ግድያ ለማውገዝ በርካታ ሰላማዊ ሰው መውጣቱን ጠቅሰው #የተወሰኑ ቡድኖች ግን አዝሚሚያቸው ሌላ ነበር ብለዋል።

ከእነዚህ የተወሰኑ ግለሰቦች መካከልም #ቦምብ ይዘው የነበሩ በህብረተሰቡ ትብብር መያዛቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በፒያሳና በመርካቶ #ለዝርፊያ የሚቃጡ ግለሰቦች እንደነበሩ ነው የጠቀሱት።

የተወሰኑት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ ጠብመንጃ ለመንጠቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር #ግብግብ ገጥመው ነበር ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአምስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ይህ ግርግር ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ #እንዳይሳካ #ታስቦበት የተከናወነ መሆኑን ነው ያነሱት።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ልጅ ከሰንዳፋ ከ3 ሳምንት በፊት ነው የጠፋው ያያችሁት ሰዎች እባካችሁ እናቱ ወ/ሮ አለሚቱ ተጨንቀዋል እና የቻላችሁትን ጥረት አድርጉ፦ 0913448370

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fana Live! የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር መገለጫ እይሰጡ ናቸው።
ተራዝሟል⬆️የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ተራዝሟል። የምዝገባውን ጊዜ ወደፊት አሳውቃለሁ ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

©ABUKI
@tsegabwolde @tikvahethiopia