TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️በቅርቡ አንድ ክፍል #ኮንዶሚኒየም የተገዛላቸው #ያብስራ እና #እናቷ ሌላ 230,000 ብር በGo Fund me የተሰበሰበላቸውን ገንዘብ በአቶ ጌታቸው ንጋቱ አማካኝነት ለአዲሱ ዓመት ስጧታ ተብርክቶላቸዋል።

©ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ፖሊስ⬆️

"ሰላም ፀግሽ! ወረዳ 8 በተለምዶ ስሞ ማሞ አካባቢ ቀጠና 3 አቅም ለሌላቸው ልጆች #የደብተር እና #መማሪያ ቁሳቁሶች አበርክተናል እኛ የፖሊስ አባላት። አብዩ ከአዲስ አበባ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት⬇️

በሰኔ 16 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር #አብይ_አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ #ቦምብ በመወርውር በማቀበል የተጠረጠሩ ጥላሁን ጌታቸውና ብርሃኑ ጃፋር ላይ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ የክስ መመስረቻ ጊዜ ሰጠ፡፡

ቀደም ሲል አቃቢ ህግ በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ በቦምብ ጉዳት የደረሰባቸው ተጨማሪ ቃል ለመቀበልና የስልክ ልውውጥ ማስረጃን እንዲሟላ ለመርማሪ ፖሊስ መዝገቡን መመለሱንና ማስረጃዎችንም ለሟሟላት ጊዜ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት መርማሪ ፖሊስ ለፌደራል የመጀመሪ ደረጃ አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት ተጨማሪ ማስረጃውን አሟልቶ አጠናቆ ለአቃቢ ህግ መመለሱን አስረድቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን መቀበሉን በመግለጽ ይህንን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ፍርድ በቱን ጠይቋል፡፡

እስከዚያውም አቃቤ ህግ ተጠርጠሪዎቹ በእስር እንዲቆዩ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪ ጥላሁን ጌታቸውም ጨለማ ቤት እንደሚገኝ እንዲሁም በቦምብ አደጋ የደረሰብኝ በመሆኑ ህክምና እያገኘሁ አይደለም ሲል በዋስ ልወጣ ይገባል በማለት ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

መርማሪ ፖሊስም በባለሙያ እየተደገፈ አቤት ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ ለዚህም የተያዘ ቃለጉባዔ መኖሩንም ገልጿል፡፡

ጨለማ ቤት የተባለውም ጉዳይ ሐሰት መሆኑንና በአሁኑ ወቅት ጨለማ ቤት የሚባል እስር ቤት እንደሌለ ፖሊስ ለችሎት አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪ ብርሃኑ ጃፋር በበኩሉ እኔ ከተያዝኩ ብዙ ቀናትን ያስቆጠርኩ በመሆኑ እንዲሁም በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀብኝ ሲሆን አሁን የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም በማለት የዋስትና ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

አቃቢ ህግም ተጠርጣሪዎቹ የፈጸሙት ወንጀል ከባድና ውስብስብ እንዲሁም በርካታ ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ለሁለት ሰዎች ህልፈት ምክንያት በመሆኑ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት ጥያቄያቸውን ተቃውሟል፡፡

የሁለቱን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤትም የዋስትና ጥያቄያቸው በማለፍ ጥላሁን ጌታቸው ላይ እስከ መስከረም 10 ባለው ጊዜ ውስጥ #ክስ እንዲመሰርት ብርሃኑ ጃፋር ላይ ደግሞ እስከ መስከረም ዘጠኝ ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመዝገባ ጊዜ መስከረም 7 እና መስከረም 8 ነው።

©የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሻሸመኔ⬆️

ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የፔፕሲ ለስላሳ መጠጥ የጫነ መኪና ተገልብጦ በሹፌሩ ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። በአደጋው እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ የንብረት ወድሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
127,902 ቤተሰባችን ፍፁም ባልተጠባልተጠበቀ መልኩ እያደገ ይገኛል። ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በናተ ነው። ምስጋናው ባላችሁበት ይድረሳችሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ5 ሺህ 325 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች መግቢያ ቀን መስከረም 25 እና 26 እንዲሁም የአዲስት ተማሪዎች መግቢያ ቀን ጥቅምት 1 እና 2 መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ።

©የሀረማያ ሬጅስትራር ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia