TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Vacancy

Hello Tsega, We're looking to hire candidates for a new chain hotels we're setting up.Three people for now.

1. Hotel Management Assistant
2. Hotel Sales and Marketing (2 people)

They need to have fitting experiences in the hotel field.

They can contact us through 0111262921.

Thank you.
#Addis_Abeba

©Is
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከራያ ቆቦ⬆️

"ዛሬ #የሶለል በአል በራያ ቆቦ ከተማ #በድምቀት ሲከበር ውሏል። በተጨማሪም ይህን በአል በUNISCO ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ነው! DESTA ከራያ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሴት ጥንካሬ፣ ብልሀት፣ ማስተዋል፣ ብርታት እና #ተስፋ ናት። ሴት ማለት ሀገር ናት!

አዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ራኒ የማንጎ ጭማቂ በጥራት ችግር ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ቢታገድም ምርቱ ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብ ቢደረግም አሁንም ግን ምርቱ ወደ ሀገር እየገባ እንደሆነ ተግልጿል።

©አሀዱ ሬድዮ FM 94.3
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 11 ዞኖች ከተውጣጡ የሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች፣ ምሁራንና ከተለያዩ የአለም አገራት ከመጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በክልሉ ወቅታዊና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ላይ እየተወያዩ ነው።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋሙን ሪብራንድ የማድረግ ስራውን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያከናውን ቆይቶ ዛሬ የብራንዲንግ ስራውን ከሰራው ኩሽቲክ መልቲ ሚዲያ ጋር ርክክብ አድርጓል ።

©Walfa Info
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ ቴሌኮም⬇️

‹‹ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር #ማስገባት አይቻልም የሚለው ገደብ ተነስቷል፡፡››
.
.
ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡም ሆነ ከሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ የስልክ ቀፎዎችን ለማስከፈት ወደ ጉምሩክ እና ኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤቶች መሄድ እንደማያስፈልግ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የስልክ ቀፎዎች አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት በኢትዮ ቴሌኮም እና በጉምሩክ በኩል ህጋዊነታቸው እንዲረጋገጥ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ዓላማውም ህገ ወጥነትን ለመከላከል ተብሎ እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ አሰራሩም ወጥነት የሌለው፣ክፍተቶች ያሉበት እና ደንበኞችን ከማጉላላት ባለፈ የጎላ ፋይዳ ያልታየበት መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአብመድ ተናግረዋል።

ከሁለት የስልክ ቀፎዎች በላይ ወደ ሀገር ማስገባት እንደማይቻል የሚከለክለው እገዳም ተነስቷል ነው ያሉት አቶ አብዱራሂም፡፡ በመሆኑም IMI ቁጥር ያላቸውን ማለትም ደረጃውን የሚያሟሉ የስልክ ቀፎዎችን ኢትዮጵያ ውስጥ መገልገል እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም ወደየተቋማቱ መሄድ ሳያስፈልግ አዳዲስ የስልክ ቀፎዎችን #መገልገል ይቻላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በዘርፉ የሚስተዋሉ የኮንትሮባንድ እና የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመግታትም ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች ተግባራዊ ያደርጋል
ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ አብዱራሂም መረጃ የታሪፍ ቅናሽ አና የስልክ ቀፎዎችን አለማስመዝገብ ከትናንት ነሀሴ 17/12/10 ዓ.ም ጀምሮ #ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ #ቅዳሜ ነሕሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከሰዓት ከ9:00ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን #ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም እንጂ የአንድ #ብሔር ተወካይ አይደለሁም። እኔ #ወታደር ነኝ። ወታደር ደግሞ ብሔር የለውም። የሀገር ጠባቂ እንጂ የብሔር ጉዳይ አስፈፃሚ አይደለም" ጄነራል ሰዓረ መኮንን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራ⬇️

ኤርትራ በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማስተናገድ እንዲያስችላት ተጨማሪ ወደብ ልትገነባ መሆኑን ብሉምበርግ አስነብቧል።

በኤርትራ በኢነርጂና ማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ዳይሬክተር አለም ክብረኣብ ኤርትራ በቀይ ባህር ላይ የምትገነባው ወደብ በተለይ በኢትዮጵያ የሚመረተውን የፖታሽ ማዕድን ወደ ፣ ጁቡቲ እና ሶማሌላንድ ማጓጓዝ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ሶማሊያወደቡ በሚለማበት አከባቢ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን የፖታሽ ማዕድን ክምችት መኖሩን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የወደቡ ግንባታ በአምስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ወደቡ የሁለቱን አገራት የፖታሽ ማዕድን ለማጓጓዝ አዋጭ ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ከፈረሙ በኋላ በቀጠናው በጋራ የመልማት አዝማሚያ እያደገ መሆኑን የብሉምበርግ ዘገባ አመልክቷል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ⬆️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከኢትዮ-ሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት መሪዎች፣ ክምሁራን እና ከተለያዩ የክልሉ ተውካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ተሳታፊዎቹ በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ፣ የስልጣን ብልግና እና በርካታ የወንጀል ድርጊቶች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም የክልሉ ህዝብ ችግሩ እንዳይሰፉ፣ ቀጥሎም ችግሩ እንዲፈታ ላሳየው ትዕግስት እንዲሁም ብስለት የትሞላብት ውይይትና ድምዳሜ አድናቆታቸውን ገልጸው በጀመርነው መሰረት በይቅርታ እና የከፋውን ችግር ደግሞ የፍትህ ስርዓቱ በሚያስቀምጠው አግባብ
በህግና በህግ አግባብ ብቻ ሊፈጸም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይም አዲሱ አመራር ከክልሉ ህዝብ ጋር ጥልቀት ያልው ውይይት በማድረግ በክልሉ ሰላምና መረጋጋቱ ስር እንዲሰድ እንዲሁም በጀመርነው የፍቅርና የመደመር መርሃችን የክሉን ህዝብ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።

©አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ⬇️

"ሰላም ፀግሽ ለ1 ወር ያህል ከአሰበ ተፈሪ በታች ተዘግቶ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት በዛሬው ዕለት አካባቢው የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ ወደ ነበረበት መመለሱ በመረጋገጡ ሊከፈት ችሉዋል።
B ከድሬ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች!

በአቃቂ መሿለኪያ ድልድይ የሚያልፍበት ወንዝ ሙላት ምክንያት የሚፈጠሩ እንግልቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የተለያዩ የመንገድ #አማራጮችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያሳስባል፡፡

አማራጮችን ለመጠቆም ያህል፡-

1. ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ ማሳለጫ (ወደ ጎሮ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ) መጠቀም ይችላሉ።

2. ወደ መሃል አዲስ አበባ ለመሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ዋናውን አቃቂ ድልድይ መጠቀም ይችላሉ።

3. ወደ ምዕራብ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ በግራ በኩል ወደ ለቡ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ መጠቀም ይችላሉ።

4. ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች በላይ አብ ሞተርስ አለፍ ብሎ ወደ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም በመታጠፍ መስቀለኛ መንገዱን መጠቀም ይቻላሉ።

እንደሚታወቀው ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ - ቱሉ ዲምቱ አደባባይ መንገድ ለረጅም ጊዜ የከተማው የምስራቅ መውጫ በር በመሆን በማገልገሉ ምክንያት በመጎዳቱ እና የሚያስተናግደውም የትራፊክ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ወቅቱ የሚጠይቀውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ማስተር ፕላኑን ጠብቆ እንደ አዲስ በመገንባት ደረጃውን የማሻሻል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በክረምት ወራት በሚጥለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመንገዶች ላይ በሚፈጥረው #የጎርፍ ችግር ምክንያት በነዋሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ አሽከርካሪዎች ከምን ጊዜውም በላይ ሲያሽከረክሩ ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ እና ሌሎች የመንገድ አማራጮች በመጠቀም ከጎርፍ ስጋትና ከእንግልት እንዲድኑ ይመክራል፡፡

©የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
@tsegbwolde @tikvahethiopia