FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.2K photos
737 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
በኮሪደር ልማት ስራ የተገኙ እምርታዎችን ቀምረን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ እንቀሳቀሳለን - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውብ መንደሮች ኢትዮጵያ እንድትመስል የምንፈልገውን ብልፅግናዊ ምስል እየገለጡ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የፓርቲያችን የከተማ ልማት እሳቤ በጠንካራ የስራ ባህል ተሟሽቶ፣ በህዝባችን ልማት ወዳድነት ከፍተኛ አቅም አግኝቶ፣ በሀገር በቀል የግንባታ ጠበብቶቻችን ድምር ውጤት ፍሬ አፍርቶ አዲስ አበባ ላይ ውጤቱን ፍንትው ብሎ አይተነዋል ብለዋል።

በኮሪደር ልማት አቧራን አራግፈን የገለጥነው ውበት፣ ከሰራን ሁሉም ሊለወጥ እንደሚችል ያረጋገጥነው እውነት፣ ዘወትር በትውልድ ልብ ውስጥ ተስፋ እና የይቻላል መንፈስን እንደሚጭር በፅኑ እናምናለንም ሲሉም ገልጸዋል።

የተገኘውን ውጤትም በአግባቡ በማጤን እና በቀጣይ በኮሪደር ልማት ስራ የተገኙ እምርታዎችን ቀምረን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንንቀሳቀስ ይሆናል ሲሉም አክለዋል።
በአማራ ክልል የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅትእየተሰራ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ አመራሩ፣ የፀጥታ ኃይሉና የክልሉ ህዝብ በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ገምግመዋል። ኅብረተሰቡ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለማወክ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚካሄዱ የሃሰት ቅስቀሳዎች ቦታ ባለመስጠት እና ከሃሰተኛ መረጃዎች በመታቀብ ከመንግሥት…

https://www.fanabc.com/archives/258150
Live stream finished (31 minutes)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ 6 ቀን ቀረው
የዕለቱ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ 7 የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሰባት ዐበይት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀምጠ፡፡ በስብሰባው ላይ የምክር ቤቱን ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች፣ የከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር፣ የክልልና የከተማ አሥተዳደር የአደጋ ስጋት ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል። ክልሎችና…

https://www.fanabc.com/archives/258155
ማስታወቂያ
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ከታዋቂው አለም አቀፍ የስፒከር አምራች ኩባንያ ጄ ቢ ኤል ጋር በመተባበር አዲሱ የኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክ አጅግ አስገራሚ የድምፅ ጥራት ይዞ መቷል፡፡ ሙዚቃ ላዳምጥ ፣ጌም ልጫወት እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ ልመልከት ቢሉ በኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ እስከሆነ ድረስ አያሳስብም፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
Live stream finished (1 hour)
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በምህንድስና፣ በጤና እና በሃብት አሥተዳደር ዘርፍ ትምህርታቸውን በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ በዶክትሬት ዲግሪ መከታተላቸው ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ፍጹም አሰፋን (ዶ/ር) ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችና የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል።

በሦስት ኮሌጆች እና በአንድ የምርምር እና ልማት ኢንስቲትዩት የተዋቀረው ዩኒቨርሲወቲው÷ በመጪዎቹ ዓመታት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ የመሆን ራዕይ አንግቦ እየሠራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ተማሪዎች በተጨማሪ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ተማሪዎችንም አሰልጥኖ እያስመረቀ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንደሚሰራ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲተገበር በትኩረት ይሰራል ሲሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ። የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው እና ሁለተኛ ምዕራፍ ዕቅድ እየተገመገመ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የውሃና…

https://www.fanabc.com/archives/258171
ሚኒስቴሩ በጤናው ዘርፍ የተያዙ ዕቅዶች እንዲሳኩ አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሠራ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ በቀጣዩ በጀት ዓመት የተያዙ ተገልጋይ ተኮር ዕቅዶችን ለማሳካት በየደረጃ ያለው አመራር በቁርጠኝነት እንዲሠራ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አሳሰቡ፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ ተጠናቅቋል። ዶ/ር መቅደስ በማጠቃላያው ላይ ባደረጉት ንግግር÷…

https://www.fanabc.com/archives/258174