FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.1K photos
737 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ ተጀምሯል – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ መጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በርካታ ዜጎችን…

https://www.fanabc.com/archives/257000
የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የዛሬ መርሐ-ግብር የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ምሽት 2 ሠዓት ከ35 ላይ ይካሄዳል።

በዚሁ መሠረት በውድድሩ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም ይሳተፋሉ።

በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ላይ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ በቀጥታ ግማሽ ፍጻሜው የተቀላቀሉ ሲሆን፤ አትሌት ብርቄ ሀየሎም በድጋሚ ተወዳድራ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፏ ይታወሳል።
ማስታወቂያ!

#Infinix_Note40_Pro_Plus

ነሀሴ 4 ከቀኑን 10 ከሰዓት ጀምሮ በቃና ስቱዲዮ የተደገሰው ልዩ የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G የሙዚቃ እና የጌም ድግስ የትም ይሁኑ የት ማይቀርበት ነው፡፡

በተለያዩ የጌም ቶርናመንቶች አዲሱን የኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G ስልክን ጨምሮ በሽልማቶችን የሚንበሸበሹበት እነ ዲጄ ሚላ፣ዮን ዜማ፣ ፍላሽ ኪዶ፣ ዲጄ ፔርዱ፣ ሳጂ እና አብሌር በመድረኩ የሚነግሱበት ደማቅ ምሽት ተዘጋጅቷል፡፡ መግቢያ በነፃ ነው፡፡

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ካቢኔው በዋናነት የመሠረተ ልማት ሥራዎች ቅንጅት፣ ጥበቃና የአሠራር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ በስፋት ተወያይቶ አጽድቋል። የመሠረተ ልማት ሥራዎች ቅንጅት፣ ጥበቃና የአሠራር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና…

https://www.fanabc.com/archives/257008
ስታርትአፖችን ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስታርትአፖችን በአግባቡ ማስተናገድ የሚያስችል ሥነ-ምሕዳር ለመገንባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡ በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ምቹ ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለው ረቂቅ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የሁለቱ ተቋማት…

https://www.fanabc.com/archives/257011
ምክክር ኮሚሽኑ ከነገ በስቲያ በሐረሪ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሐረሪ ክልል ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም አጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀመድ ድሪር÷ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በየወረዳው ከሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት የሚሳተፉ ተወካዮችን አስመርጦ ማዘጋጀቱን አስታውሰዋል። በመሆኑም ኮሚሽኑ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ በሀረሪ ክልል…

https://www.fanabc.com/archives/257014
ለ8 ቀናት አቅደው ወደጠፈር የሄዱ ጠፈርተኞች ለሥምንት ወራት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ8 ቀናት ወደጠፈር የሄዱት ጠፈርተኞች እስከፈረንጆቹ 2025 ሊቆዩ እንደሚችሉ ተሰምቷል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት አሜሪካውያን ጠፈርተኞች ወደዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሙከራ ተልዕኮ ሲላኩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደምድር ይመለሳሉ ተብሎ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ነገሮች በተያዘላቸው እቅድ መሄድ ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡ በዚህም እስካሁን ባሪ “ቡች” ዊልሞር እና ሱኒታ ዊሊያምስ…

https://www.fanabc.com/archives/257020
በ2017 ዓ.ም የመልካም አስተዳደርና የጸጥታ ሥራዎች ላይ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ይሰራል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በ2017 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ ሥራዎች ላይ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ይሰራል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው። ውይይቱን የመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ…

https://www.fanabc.com/archives/257026
በመቐለ በ2 ቢሊየን ብር ወጪ የኮሪደር ልማት ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቐለ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በ2 ቢሊየን ብር በከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በመቐለ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የማስተዋወቂያና የመገምገሚያ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ እንደገለፁት÷ የኮሪደር…

https://www.fanabc.com/archives/257029
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለ4 ክልሎች የመድሀኒትና የህክምና መስጫ ቁሳቁሶችን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ግምታዊ ዋጋቸው ከ58 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የመድሀኒት እና የህክምና መስጫ ቁሳቁሶችን አስረክቧል። የመድሀኒት እና የህክምና መስጫ ቁሳቁሶቹ በክልሎቹ ለሚገኙ 32 የጤና ተቋማት የሚከፋፈል መሆኑ ተገልጿል። ድጋፉ የህክምና ተቋማቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ እና በሽታን…

https://www.fanabc.com/archives/257032
እየተከልን እናንብብ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሥልጣኔዎችን በተለያዩ አካባቢዎችና በተለያዩ ዘመናት አስተናግዳለች፡፡ ሁሉም ለዚህች ሀገር ዛሬ ያበረከቱት ዕሴት አለ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ ለሦስት እልፍ ዓመት ጥቂት ፈሪ ዘመን ያህል አንድ ወጥ የመንግሥት ሥርዓትና የሕይወት ዘይቤ ውስጥ የኖሩ ናቸው፡፡ በዘመን ጅማሬ የደመቀና ገናናው ሥርዓት ሃልዮታዊ ማሕቀፍን መቀየር ባለመቻሉ የመንግሥታት ገናናነት በየዘመናቱ እየኮሰመነ የማኅበረሰቡም ኑሮ እየወየበ…

https://www.fanabc.com/archives/257037
አቶ ኦርዲን የላቦራቶሪ ማሽኖችን ለጤና ተቋማት አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በከፍተኛ ወጪ የተገዙ የሲ ቢ ሲ እና ኬሚስትሪ የላቦራቶሪ ማሽኖችን ለወረዳ ጤና ጣቢያዎች እና ጁገል ሆስፒታል አስረክበዋል፡፡ አቶ ኦርዲን በወቅቱ እንዳሉት÷ የጤና ተቋማትን በግብዓት በማደራጀት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ማሽኖቹ ዜጎች የፈለጉትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል እንዲያገኙ በማስቻል…

https://www.fanabc.com/archives/257040
Live stream finished (39 minutes)
ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች የተወረሰ 800 ሺህ ሊትር ዘይት ለሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች የወረሰውን 800 ሺህ ሊትር ዘይት ለ10 የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በዛሬው ዕለት አከፋፍሏል።

በመዲናዋ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ጥቂት ነጋዴዎች መሰረታዊ የፍጆቻ እቃዎች ላይ ሕገ-ወጥ ተግባር እየፈፀሙ እንደሆነ መገለጹን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

የክፍለ ከተማው ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንዱዓለም ክብረት ፥ የምግብ ዘይቱ የተወረሰው ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ሰው ሰራሽ እጥረት ለመፍጠር ምርቱን በድብቅ አከማችተው በመገኘታቸው ነው ብለዋል፡፡
ሱፍሌ ማልት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱን እንዲያስፋፋ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል- ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱፍሌ ማልት ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት እንዲያስፋፋ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ከሱፍሌ ማልት ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶማስ ኔቪውጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኩባንያው ስላለበት ወቅታዊ የምርት ሒደት፣ተኪ ምርትን ስለማሳደግና ስለ ወጪ ንግድ እንዲሁም በቀጣይ ኢንቨስትመቱን…

https://www.fanabc.com/archives/257049
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋና ቀለማት በዚህ ሳምንት