የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የዛሬ መርሐ-ግብር የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ምሽት 2 ሠዓት ከ35 ላይ ይካሄዳል።

በዚሁ መሠረት በውድድሩ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ፣ ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም ይሳተፋሉ።

በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ላይ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ በቀጥታ ግማሽ ፍጻሜው የተቀላቀሉ ሲሆን፤ አትሌት ብርቄ ሀየሎም በድጋሚ ተወዳድራ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፏ ይታወሳል።