FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.1K photos
736 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 610 ኪሎ ግራም ካናቢስ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ ጆባ ቀበሌ 610 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ፡፡ ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ ዕፅ ትላንት ሌሊት 8 ሰዓት ላይ በተካሄደ ኦፕሬሽን ከአንድ ግለሰብ ቤት የተያዘው በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ ነው በኢፌዴሪ ጉሙሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የሻሸመኔ ጉሙሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስተባባሪ ኢንስፔክተር…

https://www.fanabc.com/2-ነጥብ-4-ሚሊየን-ብር-የሚያወጣ-610-ኪሎ-ግራም-ካ/
ግሎባል አሊያንስ ከአማራ ልማት ማኅበር ጋር በመሆን በ10 ሚሊየን ብር የሐይቅ ቁጥር 2 ትምህርት ቤት ዳግም ሊያስገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል አሊያንስ ከአማራ ልማት ማኅበር ጋር በመሆን በሐይቅ ቁጥር 2 ትምህርት ቤት በ10 ሚሊየን ብር ወጪ አራት ህንፃዎችን ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ። ወራሪው ኃይል የዕውቀት ማዕድ የሚያቋድሱትን ትምህርት ቤቶች ቢያወድምም በመተባበር ከቀደመው አገልግሎታቸው የተሻለ በማድረግ እንገነባቸዋለን ሲል አርቲስት ታማኝ በየነ ገልጿል። የአማራ ልማት ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ…

https://www.fanabc.com/ግሎባል-አሊያንስ-ከአማራ-ልማት-ማኅበር-ጋ/
በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የበርካታ አገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች መገኘታቸው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለዓለም የሚያሳይ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የበርካታ አገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች መገኘታቸው የኢትዮጵያን ሰላማዊ ነባራዊ ሁኔታ ለመላው ዓለም የሚያሳይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ብርቱካን አያኖ ገለጹ። በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረው 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ መልኩ በመከናወን ላይ ይገኛል። በጉባኤው ለመሳተፍም የበርካታ…

https://www.fanabc.com/በህብረቱ-የመሪዎች-ጉባኤ-ላይ-የበርካታ-አ/
ወጣቶች እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለበጎነትና መልካምነት በማዋል በሃገር ግንባታ ውስጥ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል – አቶ ታዬ ደንደአ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ የበጎ ፍቃድ ወጣቶች ምረቃ መርሃ ግብር በጅማ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል። በስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ታዬ፥ ወጣቶች የራሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የማህበረሰቡም ጭምር እንደሆኑ ሊያውቁ ይገባል…

https://www.fanabc.com/ወጣቶች-እውቀታቸውንና-ጉልበታቸውን-ለበ/
489 ወጣቶችን የሥራ ልምምድ ለማስጀመር የመጀመሪያው ዙር የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በከተሞች የምግብ ዋስትና እና የሥራ ፕሮጀክት የተዘጋጀ የሥራ ልምምድ የመጀመሪያ ዙር ፕሮግራም 489 ወጣቶች ለ10 ቀን የሕይወት ክህሎት ማጎልበቻ ሥልጠና በመስጠት ተጠናቋል፡፡ ፕሮጀክቱ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያቶች ባቋረጡ እና ሥራ በሌላቸው ወጣቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከሠልጣኞቹ 60 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡…

https://www.fanabc.com/489-ወጣቶችን-የሥራ-ልምምድ-ለማስጀመር-የመጀ/
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጅቡቲ፣ ዛምቢያና ሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ከመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጅቡቲ፣ ዛምቢያና ሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ከመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ፀሀፊ ጋር ተወያዩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ፣ ከዛምቢያው ፕሬዚዳንት ሀካይንዴ ሂችሌማ፣ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ ፈርማጆ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ፀሀፊ አሚና መሀመድ ጋር ነው የተወያዩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያደረጉት ከ35ኛ…

https://www.fanabc.com/ጠቅላይ-ሚኒስትር-ዐቢይ-ከጅቡቲ፣-ዛምቢያ/
ዳያስፖራው ያሰባሰበውን 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ‘በአይዞን ኢትዮጵያ’ መተግበሪያ ያሰባሰበውን 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል። የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ ሁሴን፥ ድጋፉን በመረከብ ለተደረገው ለልግስናው ምስጋና አቅርበዋል። የተደረገው ድጋፍ በክልሉ አሸባሪው ህውሓት በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች…

https://www.fanabc.com/ዳያስፖራው-ያሰባሰበውን-20-ሚሊየን-ብር-የሚ/
አየር መንገዱ ከአንጎላ ልኡካን ቡድን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አሥፈጻሚዎች ቡድን ከአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከሌሎች የሀገሪቷ ልዑካን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዱን ገለጸ፡፡ አየር መንገዱ ውይይቱን ያካሄደው ከአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎንለጎን መሆኑንም ነው በገጹ ባወጣው መረጃ ያመለከተው፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

https://www.fanabc.com/አየር-መንገዱ-ከአንጎላ-ልኡካን-ቡድን-ጋር/
ለሕብረቱ ጉባኤ 15 የግልና የመንግሥት ሆስፒታሎች በልዩ ዝግጅት አገልግሎት እየሰጡ ነው – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎችና ስራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ 15 የግልና የመንግሥት ሆስፒታሎች በልዩ ሁኔታ ዝግጁ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በጤና ሚኒስቴር የአፍሪካ ሕብረት የሐኪሞች ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ማራኪ መሐሪ ለኢዜአ እንደገለጹት ፥ የጤና ሚኒስቴር ለአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ለድንገተኛ አደጋ ህክምና ሰፊ ዝግጅት በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ…

https://www.fanabc.com/ለሕብረቱ-ጉባኤ-15-የግልና-የመንግሥት-ሆስፒ/
ዛሬ ምሽት ቡርኪናፋሶ እና ካሜሮን ለደረጃ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የፍሪካ ዋንጫ መርሃ ግብር መሠረት ቡርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሮን ለደረጃ ይፋለማሉ። ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ በያውንዴ አህመዱ አሂጆ ስቴዲዬም ይካሄዳል። በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ በዕለቱም ግብጽ እና ሴኔጋል ለዋንጫ ይፋለማሉ። ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…

https://www.fanabc.com/ዛሬ-ምሽት-ቡርኪናፋሶ-እና-ካሜሮን-ለደረጃ/
በኅብረቱ ጉባኤ ላይ መሪዎች የአፍሪካን አንድነት የሚያጠናክሩ ሃሳቦችን አንስተዋል- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅብረቱ ጉባዔ ላይ መሪዎች የአፍሪካን አንድነት የሚያጠናክሩና በአህጉሪቱ ላይ የሚታዩ የተዛቡ ትርክቶችን ለመቀየር የሚያስችሉ ሃሳቦችን ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። በኅብረቱ ጉባኤ ላይ በመሪዎች የተነሱ አንኳር ጉዳዮችን በሚመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። በጉባዔው መክፈቻ…

https://www.fanabc.com/በኅብረቱ-ጉባኤ-ላይ-መሪዎች-የአፍሪካን-አ/
የአፍሪካ ህብረት ጉባዔን ምክንያት በማድረግ ለመሪዎች የተዘጋጀ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ጉባዔን ምክንያት በማድረግ ለመሪዎች የተዘጋጀ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላት እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

https://www.fanabc.com/የአፍሪካ-ህብረት-ጉባዔን-ምክንያት-በማድ/
በቱሪዝሙ መስክ እንደአህጉር የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ አፍሪካውያን በአንድነት ልንቆም ያስፈልጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በቱሪዝሙ ዘርፍ እንደአህጉር ያጠላበትን ጥላ ለመሻገር አፍሪካውያን በአንድነት መቆም እና መደጋገፍ ያስፈልገናል ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ጉባዔን ምክንያት በማድረግ ለመሪዎች የተዘጋጀ የእራት ግብዣ መርሃ ግብር በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ነው፡፡ በመርሃ ግብሩ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፥ በ35ኛው…

https://www.fanabc.com/በቱሪዝሙ-መስክ-እንደአህጉር-የተከሰተው/
በአፍሪካ ኅብረት 35ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለተገኙት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ልዑኮቻቸው የተዘጋጀ መርሐ ግብር ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካውያን አፍሪካ ውስጥ የሚያካሂዱት ቱሪዝም ለባህል ልውውጥ፣ ለመግባባት፣ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና በአፍሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎች መካከል ትብብርን ለማነቃቃት ያለውን ጠቀሜታ አመላክተዋል።

#PMOEthiopia