TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፅ ነገር #2 ? ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር በባህር በር ጉዳይ የመግባቢያ ስምምነት በተፈራረመች ወቅት ሰዓታት ሳይቆጠር ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ነበረች። ከሶማሊያ ጋር ተደዋውላም  " አይዞሽ እኔ አለሁልሽ፤ በማንኛውም መንገድ አብሬሽ ቆማለሁ " ብላት ነበር። ባለስልጣናቶቿም ኢትዮጵያ ለሶማሊያን ስንትና ስንት የደም ዋጋ እንዳልከፈለች ዛሬ ደፍረው " ኢትዮጵያን እንዳለመረጋጋት ምንጭ "…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብፅ ?

ግብፅ፣ ሶማሊያን እያስታጠቀች ነው።

ሶማሊያ የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ከግብፅ እንደተሰጧትና ተጨማሪ መሳሪያዎችን በቀጣይነት እንደምትጠብቅ አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል።

ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ ሶማሊኛ የተናገሩ ባለሥልጣን ባለፉት ቀናት በመርከብ ተጭነው ወደ ሞቃዲሾ ወደብ የደረሱት የጦር መሳሪያዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

እነዚህ መሳሪያዎች የሶማሊያ መንግሥት ጦር የሚታጠቃቸው ነው ብለዋል።

ወደ ሶማሊያ የገቡት የጦር መሳሪያዎች ፦
- ፀረ አውሮፕላን ሚሳኤሎች፣
- መድፎች
- ሌሎች አነስተኛ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ተናግረዌ።

ይህንን ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለውን የጦር መሳሪያ በሞቃዲሾ ወደብ በኩል ወደ ሶማሊያ መግባቱን በተመለከተም የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ናቸው።

በርካታ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን የጦር ማሳሪያዎቹ ወደ ሞቃዲሾ ወደብ ደርሰው የተራገፉት #በግብፅ መርከብ አማካኝነት መሆኑን ዘግበዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ከትናንት እሁድ ጀምሮ የተለያዩ ዓይነት ያላቸው ከባድ መሳሪያዎች እና በጭነት መኪና ተሸፍነው የሚጓዙ ወታደራዊ ቁሶች በሞቃዲሾ ጎዳናዎች ላይ ሲተላለፉ ታይተዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣን አሁን ከገባው የጦር መሳሪያ ጭነት በተጨማሪ በቀጣይነት ታንኮችን እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ይህ እየሆነ ያለው ግብፅ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት ደርሳ ሠራዊቷን በአገሪቱ ውስጥ ለማሰማራት ፍላጎት እንዳላት መግለጿን ካሳወቀች በኃላ ነው።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሁለት የግብፅ ወታደራዊ አውሮፕላኖች የጦር መሳሪያ ጭነው ሞቃዲሾ መግባታቸው የሚዘነጋ አይደለም። #ቢቢሲሶማሊ

@tikvahethiopia