" ከምርጫ ወዲህ ከፍተኛ ጫና እየደረሰብን ነው " - ቦሮ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ድርጅት ሰኔ 16 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በክልል ምርጫ ከተካሄደ ወዲህ በፓርቲው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደደሰበት እንደሚገኝ አሳውቋል።
ፓርቲው ምን አለ ?
- መተከል ዞን 3 ለክልል ምክርቤት እና አንድ የህዝብ ተወካዩች ምክርት ቤት ወንበር ማግኘት ችለናል።
- በቡሌን ወረዳ " ተቃዋሚ ፓርቲ መርጣቹሀል " ተብሎ የፓርቲው ደጋፊዎች ፣ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች ላይ ዛቻ እና ማስራርያ እየደረሰ ይገኛል። የፓርቲ አባላትም ለእስር እየተዳረጉ ይገኛሉ።
- የተቀናጀ ወከባና ዛቻ ነው የሚደርሰው። በተለይ ከምርጫው ውጤት በኃላ።
- ቡሌን ወረዳ ላይ አባላት በተለያዩ ወቅቶች ይታሰራሉ። ከልዩ ልዩ የፖለቲካ እና ማህበራዊ ተሳትፎ ተከልክለዋል። በንግድ፣በግብርና እንዲሁም በመንግስት ስራ ላይ የተሰማሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ላይ " ተፎካካሪ ፓርቲ ደግፋቹሀል፣ መርጣቹሀል " በሚል ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርሳል።
- የፓርቲውን አባላት መብት በመንፈግ የፖለቲካ አመለካትን መሰረት ያደረገ ጫናዎች እየደረሱ ነው።
- በፓርቲው ላይ የደረሱ የመብት ጥሰቶችን የሰብአዊ መብት ተቋማት ሊከታተሉት ይገባል።
የቡሌን ወረዳ ፖሊስ ለቀረበው ክስ ምን ምላሽ ሰጠ ?
የፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ብርሀኑ ኤጄታ ፦
" በወረዳው በፖለቲካ አመለካከቱ የታሰረ ሆነ በደል የደረሰበት ግሰለብም ሆነ ቡድን የለም።
በአካባቢው የፖለቲካ ድርጅቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ ተሳትፈዋል።
ፓርቲው ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የሌለው ክስ ነው። " #ዶቼቨለ
@tikvahethiopia