TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

ከፖሊስ የተገኘ መረጃ  ፦

በአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ እና ባለሙያዎች የሆኑት ፦
- አቶ ሃብታሙ ግዲሳ
- ስምረት ገ/እግዚአብሔር (የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር)
- አቶ ዮሴፍ ባቡ (የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር)
- አቶ አቤኔዘር ቶሎሳ (የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር)
- አቶ ለሚ ሲሌ (ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር)
- ወ/ሮ መቅደስ አረጋዊ (ገንዘብ ተቀባይ)

ጳጉሜ 05/2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ ግብር ከፋይ የሆኑ ግለሰብ የ2011 ዓ.ም እና 2012 ዓ.ም የአንድ አመት ግብር ኦዲት እንዲደረግላቸዉ የሚጠበቅበትን ሰነድ ያቀረበላቸዋል።

መክፈል ያለብህ 100,000,000 ብር ነዉ ይሉታል።

ይህን ያህል " አልከፍልም ካልክ ግማሹን አስይዘህ ነዉ ይግባኝ የምታቀርበዉ " በማለት ይገልጹለታል።

ለጊዜዉ በቁጥጥር ስር ያልዋለ ግለሰብ ሂሳብ አስጨራሽ በሚል የቀረ ደላላ ጉዳዩን አስተካክላለሁ በሚል በማግባባት ለራሱ 3,000,000 ብር እና ለሰራተኞቹ ስምንት 8,000,000 ብር ለመንግስት ከመቶ ሚሊየን በመቀነስ " 13,000,000 ብር ትከፍላለህ " በማለት ያስማማሉ።

በዚህም 8,000,000 ብር #በቤተሰቦቻቸዉ አማካኝነት በመቀበል 13,000,000 ብር የመንግስት የሚከፈለዉን እንዲከፍል መተማመኛ ሲሰጡት በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ግለሰቦቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዷል።

@tikvahethiopia