#AddisAbaba

በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወታቸዉን መታደግ ተቻለ።

ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጀርመን ድልድይ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ህይወታቸዉን ማትረፍ እንደተቻለ የእሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

እናትና ልጇ በወንዝ ዳርቻ ካለዉ የጎመን ማሳቸዉ ዉስጥ ጎመን በመሰብሰብ ላይ ሳሉ በድንገት ደራሽ ጎርፍ ሊወስዳቸዉ የነበረ ቢሆንም በወንዝ መሀል ባለ ድንጋይ ጫፍ ላይ ሆነዉ ህይወታቸወን ማቆየት ችለዋል።

ይሁንና የጎርፉ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ እናትና ልጁ በጎርፉ ሊወሰዱ በተቃረቡበት ሰዓት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰዉ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸዉ የእናትና ለጇን ህይወት መታደግ እንደተቻለ ተገልጿል።

በአካባቢዉ ቀደም ሲል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህ አካባቢ ከወንዙ የሚገኘዉን ዉሀ በመጠቀም የጎመንና ሌሎች ተክሎች ማሳ የሚገኝበት ነዉ።

በአሁኑ ሰዓት የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ባለማሳዎች ተክሎቹን ለመሰብሰብ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia