TIKVAH-ETHIOPIA
“ በሁለቱ ክሶች ትላንት ነፃ ተብያለሁ ” - ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ “ የእድሜ ልክ እስራት ያስፈርድበታል ” ሲባሉበት ከነበረው ክስ ጭምር ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነጻ ተብሏል። ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም ላይ “ ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን ፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት ” የሚሉ ሦስት ክሶች…
#Ethiopia

ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ  ጋር በነበረው ቆይታ ምን መልዕክት አስተላለፈ ?

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፦

" እስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ በማዕከላዊ፣  ቂሊንጦ አያያዙ ጥሩ አልነበረም። ብዙ ችግሮችም ነበሩ። ሰው ሊታሰርባቸው የማይችሉ ፤ ዋጋ የሚያስከፍሉ የሰቆቃ ቦታዎች ናቸው።

እኛ ጋዜጠኞች ነን። ሚዲያን በተመለከተ ለሚፈጠሩ ጥፋቶች አገሪቷ የራሷ የፕሬስ ህግ አላት፤ 2001 ዓ/ም የወጣ ፤ ከዚያ በኋላም ከ2010 ዓ/ም በኋላ አዲሱ መንግስት ሲመጣ ያንን ህግ አሻሽሎ አውጥቶታል።

ግን ህጉ ምንም ሥራ ላይ አይውለም። Even ጥፋት ሰርተን ቢሆን ኖሮ ራሱ መጠየቅ የነበረብንም በፕሬስ ህጉ  ነበረ።

ትልቁ ችግር መንግስት ህግን አለማክበሩ ነው።

ኢህአዲግ እያለ ህጎቹ በጣም አፋኝ ነበሩ ፤ ነገር ግን ከህጉ ወጥቶ ሌላ ጥፋት አይሰራም ነበር።

በእነዛው አፋኝ ህጎቹ ነው ሲያግድ የነበረው። የአሁኑ መንግስት ደግሞ በጣም የተስፋፉ ህጎች አውጦቷል፤ ህጉን ግን አይጠቀምበትም።

ከህግ ውጪ እየሄደ ነው። ከህግ ውጪ ባይሄድ መልካም ነው። "


ፎቶ ፦ ፋይል

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia