TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray

" ትግራይ በሁለት ቡድን በተከፈለ ገዢ መታመስ  ይበቃት !! " - ሦስት የትግራይ ፓርቲዎች

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) ፣ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ አስመልክተው በጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም " ስልጣኑ ከመጠበቅ አልፎ አርቆ ማሰብ የማይችለው ስርዓት ችግሮቹ ወደ ህዝብ ለማላከክ የሚያደርገው ሸፍጥ በጊዜው መታረም አለበት " ብለዋል።

" የትግራይ ችግር መፍትሄ የሚያገኘው ተጠያቂነት ያለው የመንግስት ስርዓት ሲኖር ነው " ያሉት ፓርቲዎቹ " ይህ የሚሆነው ደግሞ ሁሉን አቀፍ ምክር ቤት ሲቋቋም ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። 

ፓርቲዎቹ በስም ያልጠቀሱትና " ፀረ ህዝብ " ያሉት ሃይል ችግሮቹን ወደ ህዝብ ለማጋባት የሚያደርገው ሸፍጥና አስመሳይነት ተቀባይነት የለውም መታረም አለበት በማለት አስጠንቅቀዋል። 

" የትግራይ ህዝብ ለስልጣናቸው ህልውና በማሰብ ብቻ ወደ አደገኛ እልህ ከገቡት ገዢ ቡድኖች ራሱ በማራቅ አድነቱ ጠብቆ ሊታገላቸው ይገባል " ብለዋል።

" ትግራይ በሁለት ቡድን በተከፈለ ገዢ መታመስ ይበቃት ! " ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

" ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ የቅድምያ ቅድምያ መታየት ያለበት አጀንዳ መሆን ይገባዋል " ያሉት ፓርቲዎቹ " የተጀመረው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia