🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy

“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች ምዝገባ በማጠናቀቃቸው ልጆቻቸውን ማስመዝገብ እንዳልቻሉ የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል።

“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ውሳኔውን ቀድመው ማወቅ እንደነበረባቸው ገልጸው፣ ምዝገባ እየተገባደደ ባለበት ወቅት ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስላልቻሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረው የትምህርት ቤቱ በበኩሉ፣ ልማቱን ባይቃወምም ቢያንስ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ፣ የወላጆች ቅሬታ ትክክል መሆኑን ገልጿል።

አንድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አካሌ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ/ም የቦሌ ክፍለ ከተማ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ ት/ቤት እንደማይቀጥል ገልጸው፣ ውሳኔውን ለወላጆች እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ እንደሰጧቸው አስረድተዋል።

ት/ቤቱም ለወላጆች ጥሪ አድርጎ ‘ት/ቤቱ ለልማት ይፈለጋል ባዮቹ’ ራሳቸው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ማድረጉን፣ የተማሪ ወላጆችም ውሳኔው ዱብእዳ ሆኖባቸው ብዙ ጥያቄዎች እንዳነሱ ገልጸዋል።

የወላጆችም ቅሬታ ውሳኔው የአጭር ጊዜ በመሆኑ ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስለማይችሉ እንጂ ልማቱን መቃወም እንዳልተቃወሙ ያስረዱት እኝሁ አካል፣ “ ብዙ ወላጆች እያቀሱና እያዘኑ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል።

“ እውነትም ብዙ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ጨርሰዋል። በጥራት ችግርም ፈቃዳቸው የተወሰደባቸው ብዙ ትምህርት ቤቶች ስላሉ ጫናዎች አሉ ” ሲሉም ተናግረዋል።

“ ለምሳሌ ዛሬ አንዷ ወላጅ አንድ ት/ቤት ልጇን ልታስመዘግብ ሂዳ ስታለቅስ አይቷት ዳይሬክተሩ ደወለልኝ። እጅግ ልብ የሚሰብር ነገር ነው የሆነው ” ነው ያሉት።

“ በትምህርት ቤቱ ወደ 1,300 የሚሆኑ ተማሪዎች፣ ከ200 በላይ ሠራተኞች አሉ ” ብለው፣ መንግስት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት እንደሚበተኑ ቢገልጽም በተለይ ተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው የሥነ ልቦና ጉዳት ሊጠን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት ከመንግስት አካላት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ሙከራው ይቀጥላል።

(ክፍለ ከተማው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM