TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋል። ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ እንደሆነ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ መሆኑንም ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር…
#Ethiopia : የውጭ ምንዛሬ ገደብ !

" የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር

መንግስት ከዚህ ቀደም ባሳለፈው ውሳኔ በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የባንክ የውጭ ምንዛሪ ገደብ እንዲጣል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

አሁንም ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚሰሩ በታሪፍ መፅሐፉ አንቀፅ 87.03 የሚመደቡ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንደተጠበቀ ነው ብሏል።

በተቀሩት ዕቃዎች ላይ የተጣለው የውጭ ምንዛሪ ገደብ ውሳኔ ግን ከነማሻሻያው ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ጀምሮ የተሻረ መሆኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ፦
- ለብሔራዊ ባንክ
- ለገቢዎች ሚኒስቴር
- ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ሰርኩላር ነው።

ትላንትና ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሰሩ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ያሉበት 38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ መነሳቱን አሳውቆ ነበር።

ብሔራዊ ባንክ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ እንደሆነ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ መሆኑንም ነበር የገለጸው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia