#Ethiopia #UAE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ የተፈራረሙት ስምምነት ምንድነው ?

1ኛ. በኢትዮጵያ ብር እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) ድርሀም መካከል የምንዛሬ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል።

ይህ ስምምነት 46 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊዮን UAE ድርሃም በማዕከላዊ ባንክ በኩል ለመቀያየር / ለመለዋወጥ ያመቻችላቸዋል።

ዓላማው ፦
° በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ለመደገፍ ነው።
° ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶችን የበለጠ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ነው።

2ኛ. ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ/UAE በራሳቸው ገንዘብ (በብር እና ድርሃም) ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° የንግድ ልውውጦችን በራሳቸው (በሁለቱ ሀገራት ገንዘብ) ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
° የፋይናንስ እና የባንክ ትብብርን ያጠናክራል።
° የፋይናንስ ገበያዎችን ያዳብራል።
° የሁለትዮሽ ንግድን ያመቻቻል።
° የቀጥታ ኢንቨስትመንት ያበረታታል።
° የሙያ እና መረጃ ልውውጥ እንዲኖር ያመቻቻል።

3ኛ. የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ስርዓቶችን ለማገናኘት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ልውውጦችን ውጤታማነት ያሳድጋል።
° በፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ እና በማዕከላዊ ባንኮች ዲጂታል ምንዛሬዎች ላይ ትብብር እንዲደረግ ይረዳል።
° በክፍያ መድረክ አገልግሎቶችና በኤሌክትሮኒክ ስዊች በኩል ትብብር ያደርጋሉ። በክፍያ ስርዓቶቻቸው በኩል ኢቲስዊች እና ዩኤኢስዊች እንዲሁም በመልእክት መላላኪያ ስርዓቶች በሀገራቱ የቁጥጥር መስፈርቶች በማገናኘት ትብብር ያደርጋሉ።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በአሁን ሰዓት ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር አንዷ ናት።

ሁለቱም የ #BRICS+ አባል ሀገራት እንደሆኑም ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከብሔራዊ ባንክ እና ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia