TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ፤ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የክረምት ወቅቱ ሳይጠናከር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ከተማው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እስካሁን ባለው የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር እንዲሁም ከሜክሲኮ እስከ ሳር ቤት ያለው ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል። ከዚህ ቀደም ፦ - ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ…
#AddisAbaba

" በትልቅ ቁጠባ በ33 ቢሊዮን ነው እየተተገበረ ያለው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፥ የከተማው 5ቱ ኮሪደር ስራ እየተተገበረ ያለው በ33 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ መጀመሪያ ላይ የ5ቱም ኮሪደር ስራ ሲጠና ኮንሰልታንቶችና አጥኚው ቡድን መንገድ እና የመንገድ መሰረተ ልማት የሚፈጀው ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ እንደገለጹ አስረድተዋል።

" ይህ እንግዴ በወቅቱ ጥናት ነው በዚህ ተለዋዋጭ ገበያ " ያሉት ከንቲባዋ " እስካሁን ድረስ የተጠኑትን 5 ኮሪደሮች እየተገበርን ያለነው በ33 ቢሊዮን ነው " ብለዋል።

በ33 ቢሊዮን ብር እየተተገበረ ያለው ስራም " ትልቅ ቁጠባ የተተገበረበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስራው ብክነትን በመከላከል፣ የሚወጣውን ወጪም አስፈላጊ ነገር ላይ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በከተማው አስተዳደር የሚሰሩ ስራዎችም ለኮንትራክተሮች እንዳልተሰጡ የተናገሩት ከንቲባዋ ፥ ለአብነት የሜክሲኮ መንገድ በኮንትራክተር ሳይሆን በራስ አቅም መሰራቱን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia