" ' ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል ' የሚል ግለሰብ ማስረጃ በማቅረብ ስልኩን መውሰድ ይችላል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ከግለሰቦች ሞባይል በመንጠቅ ሱቅ ውስጥ ሲያከመቹ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

አቶ ሱራፌል ቢያብል የተባሉ የግል ተበዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14  ዋና ስራ አስፈፀሚ ሲሆኑ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም  በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነበር።

በወቅት 2 ተጠርጣሪዎች በጥቁር ሞተር ሳይክል ኮድ 2 A19216 ደ.ሕ (ደቡብ ህዝብ) በሆነ 1ኛ ተጠርጣሪ እያሽከረከረ ፣ 2ኛ ተጠርጣሪ ሞተር ሳይክል ላይ ከኋላ በመሆን ከግለሰቡ  ሞባይል ስልክ ነጥቀው በፍጥነት እያሽከረከሩ ከአካባቢው ይሰወራሉ።

የግል ተበዳይ ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ያመለክታሉ።

ፖሊስም የግል ተበዳዩን አቤቱታ በመቀበል  ባደረገው ክትትል ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ከሌቦቹ የሚረከቡ 2 ተጠርጣሪዎች  በድምሩ  4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ህግን ተከትሎ ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ተከራይተው የሞባይል ጥገና የሚሰሩበት ሱቅ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ግለሰቦች ተቀምተው የተከማቹ 32 ስማርት ሞባይል ስልኮችን በኤግዚቢት ተይዘዋል።

" ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል " የሚል ማንኛውም ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያያ በአካል  በመቅረብና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia