TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ኪራይ ? የአከራይ ተከራይ አዋጅ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የቤት ተከራዮች " ኪራይ ጨምሩ ካለዚያ ለቃችሁ ውጡ " እየተባሉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩና ቃላቸውን የሰጡን ተከራዮች ፥ አከራዮቻቸው በአንድ ጊዜ ከፍተኛ የኪራይ ብር እንዲጨምሩ ያን የማያደርጉ ከሆነ አስወጥተዋቸው ለሌላ ሰው እንደሚያከራዩ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።…
#AddisAbaba

" ... የቤት አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ ነው " - ቤቶች ልማትና አስተዳደር

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ቢሮው ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በ120 ወረዳዎች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ገልጿል።

በቀሪ የ15 ቀናት ጊዜ ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ አሳስቧል።

አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ 3 ወር ድረስ ከቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ ይደረጋል ተብሏል።

ይህንን ስራ ብቻ የሚያከናውን ቡድን መቋቋሙንም ቢሮው ገልጿል።

የውል ምዝገባው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በምሽት ጭምር እየተሰጠ እንደሆነ ያመለከተው ቢሮው ፥ " የተሰጠው የምዝገባ ጊዜ በቂ በመሆኑ የቀን ጭማሪ ላይኖር ይችላል " ሲል አሳውቋል።

ቢሮው በመግለጫው ከመጋቢት 24 ጀምሮ የሚደረግ የቤት ኪራይ ጭማሪ እና ውል ማቋረጥ ክልክል እንደሆነ እና ተቀባይነትም እንደሌለው አመልክቷል።

መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን አስገንዝቧል።

#FBC
#AddisAbaba #HousingDevelopmentandAdministration
#AddisAbaba

@tikvahethiopia