#BahirDarUniversity

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ ሊያደርግ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በፀጥታ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በ2016 ዓ/ም አዲስ ለተመደቡለት የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እስካሁን ድረስ ጥሪ ሳያደርግ ቆይቷል።

ረቡዕ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በዚህም #ከሐምሌ_ወር አጋማሽ ጀምሮ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት መከታተል ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁም ፣ ትምህርት ሚኒስቴር #በልዩ_ሁኔታ ፈተና እንደሚያዘጋጅላቸው ለማወቅ ተችሏል።

የሬሜዲያል ተማሪዎቹ ያለትምህርት በመቀመጣቸው ከፍተኛ የሆነ ጫና እየደረሰባቸው በመሆኑ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ እንድነበር አይዘነጋም።

More ➡️ @tikvahuniversity