TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ🚨 " በተጣሉ ተተኳሾች እና ፈንጂዎች 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል " - የቆላ ተምቤን ወረዳ በትግራይ ማእከላይ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ተተካሾች እና ፍንጂዎች ይገኛሉ። እጅግ አስከፊውና ደም አፋሳሹን ጦርነት ተከትሎ በአከባቢው የተቀበሩትና የተጣሉት ተተካሾችና ፈንጂዎች በበርካታ ሰዎችና እንስሳት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ በማድረስ ላይ እንደሆኑ…
#Tigray

በትግራዩ ጦርነት ምክንያት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

ዛሬ ዓርብ ግንቦት 16 / 2016 በተጣለ ተተኳሽ ባል እና ሚስት ህይወታቸው አልፏል።

አደጋው ያጋጠመው በትግራይ ክልል ፣ በማእከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ምረረ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲሆን በተተኳሹ ምክንያት የባል ህይወት ወድያው አልፏል።

የሟች ሚስት ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም ህይወቷን ማዳን አልተቻለም።

የቆላ ተምቤን ወረዳ በአስከፊው እና በደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በርካታ ውግያ ያስተናገደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአከባቢው ላይ የተቀበሩና የተጣሉ ተተኳሾችና ፈንጂዎች የማፅዳ ጉዳይ ትኩረት ይሻል ብለዋል የአከባቢው ነዋሪዎች።

ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በቆላ ተምቤን ወረዳ ብቻ በተጣሉ ተተኳሾችና  ፈንጂዎች 103 ሰዎች ላይ የሞት የአካል መጉደል አደጋ መድረሱ በሚያዝያ ወር 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ሳምንት ላይ መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
                                       
@tikvahethiopia