TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢራን የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ተሳፍረውባት በነበረው ሄሊኮፕተር በደረሰው አደጋ ህይወታቸው አልፏል። ይህንንም የሀገሪቱ የመንግሥት አረጋግጧል። ከሳቸው በተጨማሪ በሂሊኮፕተር ውስጥ አብረው የነበሩት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴይን አሚር አብዶላሂያን እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል። ሮይተርስ በአደጋው ፕሬዚዳንቱ ሲጓዙባት የነበረችው ሄሊኮፕተር #ሙሉ_በሙሉ መቃጠሏን " አንድ የኢራን…
በኢራን የሂሊኮፕተር አደጋ የሞቱት እነማን ናችው ?

- የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ
- የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን
- የተብሪዝ መስጂድ ኢማም አያቶላህ አልሃሸሚ
- የምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አስተዳዳሪ ማሊክ ራህማቲ
- የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ማሄዲ ሙሳቪ
- የሄሊኮፕተሩ አብራሪ፣
- የሂሌኮፕተሩ ረዳት አብራሪ
- ቦዲጋርድ
- የበረራ አስተናጋጅ በትላንቱ የሂሊኮፕተር አደጋ ሞተዋል።

የፕሬዜዳንት ራይሲን ሞት ተከትሎ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሞሀመድ ሞክበር በ50 ቀናት ውስጥ በምርጫ አዲስ ፕሬዜዳንት እስኪመረጥ ድረስ የፕሬዜዳንቱን ቦታ ተክተው ይሰራሉ።

@tikvahethiopia