" 41 የጸጥታ አካላት ከኃላፊነታቸው #ተነስተዋል " - አቶ ሀሚድ አህመድ

ከሰሞኑን በሲዳማ ክልል ፤ የጸጥታ አካላት የግምገማ መድረክ ሲካሄድ መሰንበቱ ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ " ለህዝብ ሳይሆን ለራሳቸዉ ቆመዋል " የተባሉ አመራሮች ከስልጣን መነሳታቸው ተገልጿል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አህመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የተጣለባቸውን የስራ ኃላፊነት በአግባቡ ያልተወጡ በተለይ ህዝብን #ሲያማርሩ እና #ሲያሰቃዩ እንዲሁም የሀገርን ሀብት ሲዘርፉ የነበሩ 41 የፀጥታ አካላት ተነስተዋል " ብለዋል።

በቀጣይ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።

#በታችኛው_እርከን ላይ ያሉ የጸጥታ አመራሮች ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ይቀጥላል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ 291 ከፍተኛ አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉ ገልጸዋል።

ለመሆኑ እነማን ናቸው ከኃላፊነት የተነሱት ? በማለት ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ ዳይሬክተሩ ፤ " አሁን ላይ መግለጽ የምችለው ብዛታቸዉን ብቻ ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" በቀጣይ ቀናት ማንነታቸውን እናሳውቃችኋለን " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia