መምህራኑ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም አሉ።

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ፣ ላለፉት 2 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው የገለጹ መምህራን የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገለጹ።

መምህራኑ በቁጥር ከ1 ሺሕ በላይ ይሆናሉ።

በወረዳው በሚገኙ 52 የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩት እኚህ መምህራን ፤ ኑሯቸውን የሚገፉት በወርሃዊ ደመወዛቸው ብቻ በመሆኑ ፣ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልጆቻቸው የሚላክ ገንዘብን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ እንደተሳናቸው ገልጸዋል፡፡

የቆንጂ ቆለላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ጌታቸው ደገፋው ችግሩ መሆኑን አምነዋል።

በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር የሒሳብ ሠራተኞች ወደ ቢሮ ገብተው ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት፣ ከመምህራን ማኅበር ጋራ በመነጋገር አዲስ ሠራተኞች ተመድበው ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia