#ሞስኮ

ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሩስያ ፣ ሞስኮ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ።

አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።

ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል።

የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።

የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።

በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል።

ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።

የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል።

እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።

ቪድዮ ፦ ከሩስያ የማህበራዊ ሚዲያዎች

@tikvahethiopia