TIKVAH-ETHIOPIA
#PretoriaAggrement አሜሪካ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር እና በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤቪን ማሲንጋ ጋር ሆነው ወደ ትግራይ መቐለ ተጉዘው ከክልሉ ባለልስጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ሀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም ከሌሎች…
#USA

አምባሳደር ሃመር እና አምባሳደር ማሲንጋ በመቐለ ቆይታቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (TPLF) ሊቀመንበር የሆኑትን ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን አገኝተው ተወያይተዋል።

ውይይታቸው የፕሪቶሪያ ስምምነትን አተገባበርን የተመለከተ ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ በኩል በፕሪቶሪያ ስምምነት ውል አተገባበር ዙሪያ ብዙ ጉዳዮች ቢፈፀሙም ፦
- ከጦርነት በፊት የነበረው የትግራይ አስተዳደር ግዛት መመለስ
- ህዝብ ነፃ የማውጣት ፣
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ ፣
- ለረሃብ ለተጋለጠ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ የማቀረብ ጉዳዮች ሳይፈፀሙ ረጅም ጊዜ መውሰዳቸው ለልኡካኑ ገልፀዋል።

ተመላሽ የሰራዊት አባላት የማቋቋም ጉዳይ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም  ቀዳሚው ጉዳይ ከጦርነት በፊት የነበረው የትግራይ አስተዳደር ማረጋገጥና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስ መሆኑ ዶ/ር ደብረፅዮን መግለፃቸውና ውይይቱ በቀጣይ ለሚኖሩ ለውጦች የሃሳብ ልውውጥ እንዲደረገ መግባባት መደረሱ ለማወቅ ተችሏል። 

#TikvahFamilyMekelle
                    
@tikvahethiopia