TIKVAH-ETHIOPIA
" እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህ/ተ/ም/ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ ፤ " እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም " ሲሉ ተናግረዋል። " በትግራይ የተወሰነ አካባቢ ፣ በአማራ የተወሰነ አካባቢ ፣ በኦሮሚያ ፣ ምስራቁ ክፍልም እንዲሁ ድርቅ አለ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ይህ ምንም ጥያቄ…
#ድርቅ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቅን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ " አሁን የተከሰተው ከ77ም ያልተናነሰ ነው " በሚል ከዚህ ቀደም የተሰጡ አስተያየቶችን ኮነኑ።

" የሚታረስ መሬት እያለን የሰው ጉልበት እያለን ድህነንት እና ልመናን ጌጥ አናድርገው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ተቸግረዋል ሊያልቁ ነው ሲሉን እንደ ሽልማት አንውሰደው ኮሮና መጣ ሊረግፉ ነው አሉ ረገፍን እንዴ ? አልረገፍንም ሟርት ነው። ጦርነት ስንጀምር ታስታውሳላችሁ ረሃብ ረሃብ ረሃብ አሉ እውነት ነው እንዴ ? " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአንድ በኩል መዘናጋት የለብንም ችግር ሲመጣ ተረባርባን እንፍታው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " 6 ወር ያልፍና የታለ የሞተ ሰው ፣ የተባለው የታለ ሲባል ማፍር ያመጣል " ብለዋል።

" አንዳንዱ ከ77 ያልተናነሰ ድርቅ አለ ይላል ማለትም 1 ሚሊዮን ገደማ ሰው ይሞታል ማለት ነው ፤ አንድ ሚሊዮን ካልሞተ እየዋሸ ነው ሰውየው እኛ ደግሞ 1 ሚሊዮን ሳይሆን አንድም እንዳይሞት አቅማችን በፈቀደ እንፍጨረጨራለን ከአቅም በላይ ከሆነስ ? እሱ ምን ይደረጋል " ብለዋል

አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ከተረባረበች ቢያንስ ሰው እንዳይሞት የማድረግ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።

ከወራት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር ገብረሕይወት ገ/እግዚአብሔር (ዶ/ር) ፤ በትግራይ የከፋው ድርቅ የተከሰተው በ1951 እና በ1977 እንደነበርና አሁን ያጋጠመው ከዚህም በላይ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ፤ " በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው "  ያሉ ሲሆን ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ነው የተከሰተው ሲሉ ተናግረው ነበር።

በእድሜ የገፉ አዛውንቶችም በክልሉ ቴሌቪዥን ቀርበው መሬት እህል አላበቅል እንዳላቸውና ሁኔታው ከ1977 የከፋ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia