TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! @tikvahethiopia
ፎቶ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የከተራ በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ።

በተለያዩ የባህል አልባሳት ያሸበረቁ ምዕመናን፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና መዘምራን ታቦታቱን አጅበው ወደየማደሪያቸው በመሸኘት ላይ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፎቶዎቹን ከኢፕድ እና ከተለያየ የማህበራዊ መገናኛዎች የወሰዳቸው ናቸው።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia