#Ethiopia 🤝 #Somaliland

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ በምትወስደው የወደብ ስፍራ ላይ ልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ መቆየቱን አስታውቋል።

ትላንት የተፈረመው ስምምነት ለስራችን ትልቅ ዜና ነው ያሉት የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)፤ በድርጅቱ ስራ ላይ ትልቅ እመርታ የሚያመጣ ነው ብለውታል።

በተለይ ከዋጋ እና አላስፈላጊ ወጪ ጋር በተገናኘ እንደ አገር ትልቅ እፎይታ የሚያመጣ ነው ሲሉ ስምምነቱን አሞግሰዋል።

ድርጅታቸውም በተወሰደው ቦታ ላይ መሰረተልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ እንዲሁም የሚያስተዳድራቸውን መርከቦች መጠን ለመጨመር ሲሰራ እንደቆየ ነው የገለፁት።

ትላንት ይፋ በተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ የበርበራ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ በሚገኝ የባህር ዳርቻ የራሷን የጦር ሰፈር እና የንግድ ወደብ እንደምታለማ ተገልፀጿል።

Via CAPITAL

@tikvahethiopia