#ጥቁር_አንበሳ👏

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመርያው የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ነው የተባለለት የአንጎል የደም ስር ክሊፒንግ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ይህ ህክምና የተደረገላት ታካሚ ከአዲስ አበባ በጥቂት ርቀት ላይ የምትኖር ሲሆን ድንገት በዕለት ሥራዋ ላይ ሳለች ከፍተኝ የራስ ህመም ይሰማት እንደጀመረና ከዚያም እራስዋን ስታ መውደቋን ታሪኳ ያስረዳል።

ህክምና ተቋም እንደደረሰችም በተደረገላት ምርመራ በአንጎልዋ ውስጥ የደም ቧንቧ መፈንዳት ምክንያት የደም መፍሰስ እንደተከሰተና የፈነዳዉን የደም ቧንቧ በቅዶ ጥገና ህክምና ባስቸኳይ ካልተስተካከለ ለሞት የሚዳርጋት መሆኑን ይነገራታል።

በወቅቱ ታካሚዋ ህክምናውን ውጭ ሀገር ወይንም የግል የህክምና ተቋም ላይ ከፍላ መታክም ስላልቻለች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መላኳን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በኒውሮሰርጀሪ ዲፓርትመንት አስተባባሪነትና የአንጎል ደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ህክምና ከፍትኛ ልምድ ባካበቱት ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ የሚመራ የህክምና ቡድን ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ሶስት ስዓት ከግማሽ በወሰደ የቀዶ ጥገና የተስተካከለ የአንጎል የደም ዝውውር እንዲኖራት ማድረግ ችሏል።

ይህ ህክምና ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ደረጃ በመንግስት ሆስፒታሎች ሲሰራ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ታካሚዋ በተደረገላት ህክምና እጅጉን እንደተደሰተች ገልጻ፥ ባሁኑ ስኣት ከህመምዋ አገግማ ወደ ቤትዋ መመለስ ችላለች።

ለሌሎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያግዝ ዘንድ በቀዶ ጥገና ወቅት የተወሰዱ ፎቶዎችን ለማጋራት ታካሚዋ ፍቃድዋን የሰጠች ሲሆን ፤ በቀዶ ጥገናው ላይ የተሳተፉ አባላት ከታች እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

➡️ ዶ/ር ቶማስ ቦጋለ (የአንጎል ውስጥ የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም)

➡️ የነርቭ ቀዶ ሕክምና ሬዝደንት ዶ/ር መሃሪ ፣ ዶ/ር ፒኔል ፣ ዶ/ር ዳዊት እና ዶ/ር ብዙአየሁ

➡️ ስክራብ ነርስ ፦ ነርስ ኢብራሂም፣ ሲስተር ሶስና እና ሲስተር መንበረ

➡️ ዶ/ር ቦንሳ (አንስቴዚዮሎጂስት)

➡️ አንስቴዚዮሎጂ ሬዝደንት፦ ዶ/ር ማህደር ፣ ዶ/ር እየሩስ እና ዶ/ር ውበት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል (ቀዶ ጥገናውን ካከናወኑ የጤና ባለሞያዎች) ነው ያገኘው።

Via  @TikvahethMagazine