#ትግራይ

መሻሻል ታይቶበት የነበረው የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ሁኔታ እንደገና አሳሳቢነቱ መጨመሩ ተነግሯል።

በአንድ ሳምንታ ብቻ በሁለት ከተሞች ሁለት ሰዎች በሰለት በመወጋት እና በድንጋይ በመመታት ተገድለዋል።

በአሰቃቂ አገዳደል ህይወታቸው ያለፈው የዓዲግራት እና የሽረ እንዳስላሰ ከተሞች ወጣት ነዋሪዎች ናቸው።

የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እስከ አሁን ባለው መረጃ በሟቾች ተጠርጥሮ አስከ አሁን በቁጥጥር ስር የዋለ የለም።

ሟች የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ  ደስታኣለም ነጋሽ ከቤተሰቡ አምሽቶ ወደ ቤቱ በመኪና ሲጓዝ ፤ የመኪና መንገድ በድንጋይ ዘግተው በማውረድ ዘራፊዎቹ ሲገድሉት አብሮት የነበረ ሌላ ሰው ሊያመልጥ ችሏል።

ግድያው የተፈፀመው ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት  አከባቢ ነው። 

ሟች ወጣት ጋይም የሽረ እንዳስላሰ ከተማ ነዋሪ ነበር። ከጓደኞቹ ሲዝናና አምሽቶ ወደ ቤቱ ሲጓዝ በከተማው ቀበሌ 02 ልዩ ቦታ ማይ ሎሚን ሆቴል በተባለ አከባቢ በስለት ወግተው በድንጋይ ደብድበው ጥለውት አመልጠዋል።

ወጣት ጋይም ህይወቱ ሳታልፍ ሰዎች ደርሰው ወደ ሆስፒታል ሊመውሰድ ቢጥሩም የደረሰበት ድብደባ ከባድ ነበርና መትረፍ አልቻለም። አሰቃቂ ግድያው የተፈፀመው ታህሳስ  8/2016 ዓ.ም ነው።

ታህሳስ 9 እና 10/2016 ዓ.ም የአክሱም ከተማ ነዋሪ የአይን እማኞች እንደሚሉት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አከባቢ የተደራጁ ሌቦች ሁለት ሰዎች በመደብደብ 25 ሺህ ብር ቀምተዋቸዋል።

ታህሳስ 9 /2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ቀበሌ 17 ልዩ ቦታ ዕዳጋ ብዕራይ (የበሬ ገበያ) በቡድን በመሆን በሬ ሰርቀው ለማረድ ሲሞክሩ ባሰማው ድምፅ በመፍራት ዘራፊዎቹ ሲያመልጡ በሬው በፓሊስ እጅ ገብቶ ባለቤቱ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

የተለያዩ የትግራይ ከተሞች ነዋሪዎች " ከሚታወቁት የማይታወቁት የዝርፍያና የግድያ ወንጀሎች በርካታ ናቸው " ይላሉ ፤ ስለሆነም የከተሞች የፀጥታ ጉዳይ እጅግ በጣም ትኩረት እንደሚሻ በአፅንኦት አሳስበዋል።

የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በዚህ ዙሪያ የሚለው ካለ ለማስተናገድ ዝግጁን የሚሰጠው መግለጫ ካለም ተከታትለን እናቀርባለን።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                                      
@tikvahethiopia