#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ ዉስጥ ያለዉ ህገወጥ እንቅስቃሴ ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር ሆኖ በሰራዉ ስራ ከፍተኛ ለዉጥ ቢታይም አሁንም ችግሮች መኖራቸዉ ተገለጸ።

በከተማዉ ባሉ የታክሲ መሳፈሪያና መዉረጃ አካባቢዎች የስልክ ነጠቃና ስርቆት እንዳማረራቸዉ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ በዚህ መልክ የተዘረፉ ስልኮች በገበያ ዉስጥ በግልጽ ሲሸጡ እንደሚታይ ይናገራሉ።

አሁን ላይ የተሰረቁ ስልኮችን በግልጽ በከተማዉ ዉስጥ ባሉ የገበያ መግቢያዎች ሲሸጡ እንደሚታይ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ ይህ ጉዳይ ሀይ ሊባል እንደሚገባ በመግለፅ የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ የሰጠዉ  የከተማዉ ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታዎችን ለማስተካከል በአዲስ አደረጃጀትና ተልእኮ ከተማዋን የተሻለ ሰላም ያላት ለማድረግ  እንደሚሰራ  ገልጿል።

በቅርቡ ወደስልጣን የመጡት የሀዋሳ ከተማ ጸጥታ ጉዳይ ሀላፊዉ አቶ ወንድሙ ቶርባ ሁኔታዉን ለማስተካከል ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን በከተማዉ ነዋሪ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ገልጸዋል።

ይህ የማህበረሰብና የፖሊስ የትብብር አንቅስቃሴና ስምሪት  በደመራ በአል በስፋት የተስተዋለ ሲሆን ወጣቶችና ፖሊስ በመቀናጀት ዉጤታማ ስራ ሲሰሩ መታየታቸዉን በቦታው የሚገኙ የቲኪቫህ ቤተሰቦች ተመልክተዋል።

@tikvahethiopia