" ካለፈው ሃምሌ ወር አንስቶ በትንሹ 183 ሰዎች ተገድለዋል " - ተመድ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ዛሬ ማክሰኞ መግለጫ አውጥቷል።

ምን አለ ?

- በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ መባባሱ በጣም ያሳስበናል ብሏል።

- ከሀምሌ ወር አስቶ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች መገደላቸውን ካሰባሰብነው መረጃ መረዳት ችለናል ሲል ገልጿል።

- አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሰዎች መታሰራቸው መረጃ ደርሶናል ፤ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የፋኖ ደጋፊዎች ተብለው የተጠረጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጅ ወጣቶች ናቸው ብሏል። ከነሃሴ መጀመሪያ አንስቶ የቤት ለቤት ፍተሻ ሲደረግ እንደነበር ፤ በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ ሲዘግቡ የነበሩ 3 ጋዜጠኞችም መታሰራቸውን ገልጿል።

- እስረኞቹ መሰረታዊ ነገሮች በሌላቸውና ምቹ ባልሆኑ የማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንዲቀመጡ መደረጉ አመልክቷል።

- ባለሥልጣናት የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ ማንኛውም የነፃነት መነፈግ ድርጊት በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩ እንዲፈቱ ጠይቋል።

- ባለሥልጣናት የታሰሩ ሰዎች ሁኔታ ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና ደረጃዎችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው እንዲሁም የተመድ የሰብአዊ መብት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተቆጣጣሪ አካላት ሁሉንም የእስር ቦታዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያዩ እንዲፈቅዱ ጠይቋል።

- በተወሰኑ የአማራ ክልል ከተሞች የፌደራል ሃይሎች መኖራቸውን ተከትሎ የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ማፈግፈጋቸውን የገለፀው ተመድ ሁሉም ተዋናዮች ግድያ፣ ጥቃትና ሌሎች ጥሰቶች እንዲያቆሙ ጠይቋል። ቅሬታዎች በውይይት እና በፖለቲካ ሂደት መፍታት አለባቸውም ብሏል።

- በምዕራብ ትግራይ አወዛጋቢ ቦታዎች ከ250 የማያንሱ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ፖሊስ፣ በአካባቢው ባለስልጣናት እንዲሁም በአካባቢው ታጣቂዎችና በታጠቁ የወልቃይት ተወላጆች ባካሄዱት ዘመቻ መታሰራቸውን ገልጿል። በኃላም ወደ ትግራይ ጊዜው አስተዳደር ስር ወዳለ አካባቢ በታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች እየተወሰዱ ሳለ በመከላከያ ሰራዊት እጅ መግባታቸውና በኃላም መከላከያ ልየታ አደርጎ የትግራይ ተወላጆቹ ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዲመለሱ ወይም እዛው በጊዜዊ አስተዳደሩ ስር ባለ አካባቢ እንዲሆኑ የሚል ምርጫ እንደሰጣቸው ገልጿል።

- በኦሮሚያ ክልልም የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ወንጀሎች መቀጠላቸውን በማመልከትም በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል።

(የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት)

@tikvahethiopia