#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን #በውድድር መሆኑን አስታውቋል።

ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን " በልዩ " ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 16፤ 2015 በዋናው ቅጥር ግቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር " ሁለት ዓመት ባልሞላ " ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታውቀዋል።

መረጃው የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር እና የኢዜአ " ነው።

@tikvahethiopia