#OFC #OLF

ቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከእያንዳንዳቸው 50 በመቶ ተወካዮችን ይዘው ለመቅረብ እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።

የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከሰሞኑን ከ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ቃለ ምልልስ ፓርቲያቸው በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕ/ር መረራ ፤ መንግሥት አሁን ላይ እየሄደበት ባለው መንገድ ወደፊት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ይደረጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጻዋል።

ያም ሆኖ ግን ለምርጫው ከኦነግ ጋር ስምምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

፣ ከእኛ ሃምሳ በመቶ ከእነሱ ሃምሳ በመቶ ተወካዮችን አዘጋጅተን በምርጫ ለመምጣት ዕቅድ አለን፡፡ " ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲያ "  ከኦነግ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዲሁም የኢህአዴግን ስርዓት በመጣል ውስጥ ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸው የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በምን ምክንያት እንደጠፉ የተጠየቁት ፕ/ር መረራ ምላሽ ሰጥተዋል።

" እኔ እንደምገምተው የፖለቲካ ምኅዳሩ አልተመቸውም፡፡ " ያሉት ፕ/ር መረራ " የፖለቲካው ምኅዳር ጠቦበታል፣ በዚህ በኩልም እሳት ነው ፤ በዛም እሳት ነው መንግሥትም እሳት ሆነበት  " ሲሉ መልሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እሳቸው እና የሚመሩት ፓርቲ ከመንግሥት ጋር አብሮ እየሰራ ነው የሚባለው ወሬ ሀሰት መሆኑና ከመንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ፕ/ር መረራ ጉዲና ለጋዜጣው ተናግረዋል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦
- አሁን ላይ ዝምታ መርጠው ስለጠፉበት ሁኔታ፤
- ስለ ኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ፤
- በኦሮሚያ ክልል ስላለው ቀውስ እና ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ፤
- ስለ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና የመንግስት ድርድር፤
- ስለ ህገመንግስት መሻሻል ፤
- በኦሮሞ እና በአማራ ፖለቲካ ስላለው ሁኔታ፤
- ስለ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ምላሽ የሰጡበት የ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ቃለ ምልልስ በዚህ ይገኛል ፦ http://www.ethiopianreporter.com/

@tikvahethiopia