TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከምባታጠምባሮ

የዱራሜ ከተማ የምክር ቤት አባላት በሙሉ እየተደራጀ በሚገኘው ክልል ያለውን የቢሮ ክፍፍል ተቃወሙ።

አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል።

የምክር ቤት አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡት በ2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የምክር ቤት አባላት ምን አሉ ?

አዲስ እየተደራጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም ያለማግኘት እና ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል በመሆኑ በፍጹም መታረም ያለበት ነው ብለዋል።

እኩል የመልማት ፣ የመበልፀግና የማደግ መብት እንዲከበርም ጠይቀዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ  ክልል " የክላስተር አደረጃጀት ያለው ኢ-ፍትሃዊ አደረጃጀትን በሙሉ ድምፅ በመቃወም ፤ በቀጣይ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ በመጠየቅ አስቸኳይ ጉባኤያቸውን አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ በቢሮ ክፍልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የዱራሜ ነዋሪዎች ሰኞ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰልፉን የሚያስተባብረው አካልም ከከተማው ፍቃድ እንዳገኘ ተሰምቷል። በዚህም ሰኞ ጥዋት ከ3 እስከ 5 ድረስ በዱራሜ ኢፍትሃዊ ነው የተባለውም የተቋማት ክፍፍል የሚቃወም እና ማስተካከያ እንዲደረግበት የሚጠይቅ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia