TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል። የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል። በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ…
#GONDAR

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና ዶክተር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በከተማው ስላለው ሁኔታ መረጃዎችን አጋርቶናል።

- ታማሚዎች በኦክስጂን እና ደም እጥረት እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።

- ለአምቡላንስ ጨምር ምንምአይነት የትራንስፖርት አማራጭ እንደሌለ ፤ ታማሚዎች በሰው ኃይል በሸክም ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ መሆኑን አስረድቷል።

- ወደ 20 (ሰላማዊ ሰዎች) ወደ ሆስፒታሉ ከደረሱ በኃላ እንደሞቱ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደሚጡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ገልጿል።

- በርከታ ሰዎች በቤታቸው ሞተው፣ ቀብራቸውም በአካባቢያቸው በተለይም በቀበሌ 4 ፣ 12 ፣ 11 እና 18 መፈፀሙን አመልክቷል።

- ባለፈው ሰኞ በነበረ ግጭት ከሆስፒታሉ የተወሰኑ ህፃዎች በመሳሪያ ቢመቱትም የተጎዳ ሰው ግን እንዳልነበር ገልጿል።

- ሆስፒታሉ ምግብ እንዲሁም መድሃኒት እያለቀበት መሆኑን አመልክቷል።

ዛሬ ጎንደር እንዴት ናት ?

አሁን ላይ በጎንደር ከተማ ከየትኛውም አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ አይደለም። ጥዋት ላይ ለጥቂት ሰከንድ ፒያሳ እና ቀበሌ 18 አካባቢ ተኩስ ተሰምቶ ነበር።

ከትላንት ማታ አንስቶ ዛሬም ጥዋት በከተማው አብዛኛው ክፍል ላይ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለ ሲሆን ሰራዊቱ በሆስፒታሉ አካባቢም መኖሩን ይኸው ዶክተር ገልጿል።

የህክምና ዶክተሩ ከምንም በላይ በሆስፒታል ያለው የኦክስጅን ፣ የደም እጥረት እንዲሁም የአምቡላንስ ትራንስፖርት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ #ጎንደር ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ ግጭት ካስተናገዱ የአማራ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ ናት።

@tikvahethiopia