#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው እርዳታ በተወሰነ መልኩ ማቅረብ መጀመሩ ተገለፀ።

በተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ እርዳታ ከአምስት ወራት ብኋላ እጅግ አነስተኛ በሚባል መልኩ እርዳታ መላክ መጀመሩን " አሶሸትድ ፕሬስ " ገልጿል።

ድርጅቱ ለአሶሸትድ ፕሬስ እንደገለፀው ፤ በትግራይ 4 አካባቢዎች በመቶ ሺህ እርደታ ፈላጊ ዜጎች ላይ አዲሱ የተቋሙ አሰራር ትግበራ ሙከራ በሐምለ መጨረሻ መጀመሩን አሳወቋል።

የተለያዩ ተቋማት ፣ ሃይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ አካላት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለተቸገሩ ወገኖች ሲያቀርብ የነበረው  እርዳታ ማቋረጡን ተገቢ አለመሆኑ እና ከሞራል አንፃር ኢሞራላዊ ነው ብለው ሲተቹት እንደነበር ያወሳው ዘገባው በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ በምግብ እጦት ምክንያት በትግራይ የሞት አደጋ ማጋጠሙን አስታውሷል።

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት / USAID ኃላፊ የሆኑት ሳማንታ ፓወር በበኩላቸው ፤ " ተፈጠሩ የተባሉ ችግሮችን በማጣራት እንዲሁም እርዳታው ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በትክክል መድረሱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው " ያሉ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታው በአጭር ግዜ ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል ማለታቸው ተዘግቧል።

ከአምስት ወራት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ  ድጋፍ ስርቆትና ላልተገባ ተግባር ውሏል በመባሉ እንዲቆም መደረጉን የሚታወስ ነው።

መረጃው የድምፂ ወያነ ነው።

@tikvahethiopia