TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#ጎንደር

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የገቡ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትላንት ሰዓት እና የዛሬውን ፈተና እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ፤ በማራኪ ፣ ቴዎድሮስ ፣ ፋሲል ግቢ ለፈተና የገቡ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ፈተናቸውን ሳይወስዱ እንደቀሩ አመልክቷል።

በዕለቱ በነበረ የተኩስ ልውውጥም 1 ፈታኝ / የፈተና አስፈፃሚ እና 2 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፤ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ደግሞ ቆስሏል።

በአጠቃላይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ፈተናቸውን መፈተን ያልቻሉ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ በሚመቻችላቸው መርሐ ግብር ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጎንደር ካጋጠመው ችግር ውጭ በሌሎች የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም ፈተና ተሰጥቶ መጠናቀቁን አሳውቋል።

@tikvahethiopia