TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል። ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር። ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ…
#ኦዲት

" በ86 የመንግስት መስሪያ ቤቶች 6 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ነው ተመላሽ የሆነው " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ፤ የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ ስለመጣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰቡ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህ ያሳሰቡት ከቀናት በፊት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፓርላማው የ2014 ዓ/ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ክንዋኔ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት ዓለማ በትክክል እንዲውል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " የክዋኔ ኦዲት ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ የሪፖርቱን ተአማኒነት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ይገባል " ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ እና ሪፖርት በወቅቱ በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በይበልጥ ጥረቱን አጠናክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አስፈጻሚው አካል ለኦዲት ግኝቶች ትኩረት ባለመስጠት የገንዝብ የመመለስ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተቋማትን በመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ የመጣ በመሆኑ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

የፌደራል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው ፤  " በ86 የመንግስት መ/ ቤቶች 6 ቢለዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ተመላሽ በመደረጉ የሚፈለገውን ለውጥ እያመጣ አይደለም።  " ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ ፤ በተወሰኑ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ባባከኑ የስራ ኃላፊዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

#HoPR

@tikvahethiopia