TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OLF50

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለው ?

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ፤ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ አማካኝነት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው  መግለጫ ወቅት ፓርቲው መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ ስለሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) የታጠቀ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥቷል።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ምን አሉ ?

" የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር አሁን ላይ ግንኙነት አለው ወይ ለሚለው፤ ያ ሰራዊት የፖለቲካ ጥያቄ ያለው ሰራዊት ነው፡፡

አባላቶቹን ለምን እንደሚታገል አስተምሮ ነው ወደ ጦር የሚያሰማራው፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ደግሞ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ ይህን ትግል #በሰላማዊ መንገድ እያካሄደ ነው፡፡

ይህ መንግስት አለመግባባቱ በተፈጠረ ጊዜ ኦነግን ገመድ ውስጥ አስገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን ነው የጠየቀው፡፡ ትጥቅ አልፈታም ያለው ያ ሰራዊት የኔ ነው ወይስ አይደለም እንድንል፡፡

በወቅቱ ከአባገዳዎች ጋር ሆነን በኦሮሞ ባህል ማዕከል ባደረግነው ጉባኤ መንግስት ስምምነቱን አፍርሷል ብለን በማመናችንና ጦሩን ማስገባት ስርዓት ስላለው እኛ በወቅቱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለአባገዳዎች ሰጥተን ነው ከመሃል የወጣነው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከጦሩ ጋር ግንኙነት የለውም፡፡

ያን ተከትሎ በምርጫ ቦርድ በሕጋዊ መሰረት ብንንቀሳቀስም ይሄው ቤት ውስጥ እስከመታገት የሚደርስ ጫና ደርሶብናል፡፡ የኦነግ እንቅስቃሴ ግን በተለያየ መንገድ ቀጥሏል እንጂ አይገታም፡፡

አሁንም የምንጠይቀው መንግስት ሰላም እንዲወርድ ተቀምጦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ግደታውን ይወጣ።

በኦሮሚያ ለሁሉም ዜጋ እኩል ክብር እንዲሰጥና መከባበር እንዲሰፍን እንጠይቅላለን። "

@tikvahethiopia